ምርጫውን የሚረብሹ ኃይሎች

ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር መፍትሔ አላገኘም ማለት ይቻላል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንጂ እየተሻለ አልመጣም። ዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት ከተቸገሩ ቆይቷል። በተለይም ያለፉት ሦስት የለውጥ ዓመታት በአገሪቱ ታሪክ ከባድ የሚባል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል። ኮሮና ቫይረስ ሳይከሰት በፊት ዩንቨርስቲዎች ዋና የግጭት መንስኤ እንደነበሩ የሚታወስ ነው። ጽንፍ የረገጡ ፖለቲከኞም ዩንቨርስቲዎች ላይ ትኩረት አድርገው ነበር።

በፀጥታ ችግር ተማሪዎች ከተበተኑበት ዩንቨርስቲ መካከል ሐሮማ ዩንቨርስቲ አንደኛው እንደነበር ይታወሳል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በሐረር ቤተ እምነቶች ተጠግተው ነበር። ኮሮና ተከስቶ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው ከተሸኙ በኋላ አስቀድሞ ሲነገር የነበረው የዘር ማጥፋት አጀንዳ ተፈጽሟል። አሁን ደግሞ ወደ ቤተ እምነቶች ተሰማርቷል። በብሔር እና በሃይማኖት የተቀናጀ ጥቃት ይፈፀማል የሚል ሥጋት በብዙዎች ዘንድ ተስተጋብቷል።

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ተሞክሮ የከሸፈው ሃይማኖት ተኮር ግርግር በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለዘመናት ተከባብረው በኖሩ ቤተ-እምነቶች መካከል ጠብ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ቢያንስ ለሁለት ዓላማ መሆኑ ይታወቃል። የመጀመሪያው እና ትልቁ ጉዳይ በቀጣይ የሚደረገውን ብሔራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ ነው። ሁለተኛው አገሪቱ ተስፋ ያደረገችበትን እና ሀብቷን የገበረችበትን የሕዳሴ ግድብ ለማስተጓጐል ነው።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*