
በሐረሪ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንደተደረገው ሁሉ በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ እየተዘዋወረ ይገኛል።
በዋንጫው ርክክብ ወቅትም የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንደተናገሩት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሀገራችን የእድገት ውጥኗን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በሂደት ላይ ፕሮጀክቶች ቀዳሚው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከግድቡ ግንባታ ጅማሮ መላው ህዝብ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን በእውቀቱ፣ በገንዘቡና በጉልበቱ አስተዋፅኦ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ክልሉ ከመጣ ወዲህም ህዝቡ በንቃትና በከፍተኛ መነሳሳት በመንቀሳቀስ ግድቡ እንዲጠናቀቅ ድረስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
Be the first to comment