
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ ‹የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ሥጋት ሆነዋል› ያላቸውን በርካታ ግለሰቦች ይዞ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ውስጥ፡- በቀንም ሆነ በሌሊት ዝርፊያ የሚፈጽሙ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ሰዎች ላይ የእጅ ስልክ፣ የአንገት ሐብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው የሚሰወሩ እንደሚገኙበት ተነግሯል።
በተያዙት ግለሰቦች ላይ በተካሄደው ምርመራ፣ ምርጫውን እና የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን የማደናቀፍ ዓላማን ያነገቡ› መሆናቸውም ተጠቁሟል። በብዙ ምክንያት የአገሪቱን ሰላም እና ፀጥታ በማደፍረስ፣ ‹የአገር ገጽታን ለማጠልሸት› መዲናዋ ‹አሸባሪ› ለተባሉ አካላት ዋነኛ ትኩረት መሆኗም ተዘግቧል።
ከሰሞኑ የተያዙት የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል፣ የሽብር ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ሥጋት የሆኑ ግለሰቦች መሆናቸውን፣ የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። እንደ ፖሊስ ኮሚሽኑ ገለጻ፡- ከሕዝብ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት፣ በጥናት ላይ በመመስረት፣ በሰባት ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22/2013 ዓ.ም ባከናወነው ኦፕሬሽን፣ ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦችን ይዞ የወንጀል ም ርመራ ጀምሯል።
Be the first to comment