
አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ርዕስ-መዲና ናት። የበርካታ አገራት ኢምባሲዎች መገኛም ናት። የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በስፋት ይስተናገዱባታል። ሰሞነኛ መስተንግዶዋ ግን ከወትሮው የተለየ ነው። ይህም ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ ነዋሪዎቿ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገቡ ይመስላሉ።
ስለ ዴሞክራሲ የተሻለ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ይገኛሉ። መራጮች ለአገርም ሆነ ለከተማዋ የሚበጀውን ፓርቲ የመምረጥ ግንዛቤ አላቸው ተብሎ ይታመናል። የተወዳዳሪ ፖለቲከኞች ትንቅንቅ ቀላል የማይሆነውም ለዚህ ነው። አሁን ላይ ከተማዋ ከአገር ውስጥ እስከ ዓለም-ዐቀፋ ድረስ ትኩረት ተደርጎባታል ማለት ይቻላል።
በተለይም ከተማዋ ከምርጫ ጋር የተገናኘ ታሪኳ አሳዛኝ ከመሆኑ አኳያ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ የደረሰባት ፖለቲካዊ ቀውስ በታሪክ የሚዘነጋ አይደለም። የዘንድሮው ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከእስከዛሬው የተለየ የሚያደርገው ከለውጥ በኋላ በመሆኑ ነው። ይህም የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይገመታል።
Be the first to comment