ከመረጋጋት ወደ ሰላም ስጋት ምልክቶች

ቶ ሙስጠፋ መሀመድ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ፣ ክልሉ ለሌሎች አርአያ የሚሆን መረጋጋት እንደሰፈነበት ሲነገር ይደመጣል። በተለይም ከቀድሞ የክልሉ መሪ አቶ አብዲ ኢሌ አስተዳደር ዘመን የነበረውን የዜጎች መገደል፣ መሳደድና ህገወጥ ድርጊቶች መሻሻላቸው ለብዙዎች አስገራሚ ነገር ነበር። በዚህም አቶ ሙስጠፋን በተጨማሪ በሃላፊነት ላይ ያሉ አመራሮች ከሁሉም አቅጣጫ ምስጋና ሲቸራቸውም ይሰማል።

ይሄ መረጋጋት ለሰስት ዓመታት ቢዘልቅም፣ አሁን አሁን የሰላ ስጋት ምልክቶች እየተመለከትን እንገኛለን። በተለይም ሀገራዊ ምርጫው ቀን ተቆረጦለት በያዝነው 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከተገለጸ እና የመራጮች ምዝገባና የፖለቲካ ድርጅቶች የምርጫ ቅስቀሳን ተከትሎ የአካባቢው ፀጥታ መነቃነቅ መጀመሩ እየተስተዋለ ነው። በምርጫ ጣቢያዎች ከመከፈታቸውና ከአፋር ክልል ጋር ካወዛገበው ጉዳይ አንስቶ እስከ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ምዝገባ ላይ የሚታየው ያልተገባ አሰራር ተጠቃሶች ናቸው። እንዲሁም በያዝነው ሳምንት ደግሞ በክልሉ የሽብር ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸው የክልሉ ሰላም ላይ ጥላ ያጠለበት ክስተት ሆኗል።

ለሽብር ጥቃት ተሰማርተው በነበሩ አካላት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጠው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በጅግጅጋ ከተማ የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ ነበሩ ያላቸውን 9 ግለሰቦች ይዤያለሁ ብሏል። ግለሰቦቹ በተለያዩ የእምነት ተቋማት ላይ ጥቃት በማድረስ እምነትን መሰረት ያደረገ ብጥብጥና ሁከት እንዲከሰት ሲሰሩ መቆየታቸውን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*