የክልሎቹ የምክክር መድረክ

በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አወሳኝ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት የታሰበ የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ሰሞኑን ተካሂዷል። በሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ይህ የምክክር መድረክ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን መገምገሙ ታውቋል።

የምክክር መድረኩ በሁለቱ ክልሎች ተጎራባች ወረዳዎች፤ ባለፉት ጊዜያት በሰላምና ፀጥታ ላይ በጋራ የተከናወኑና በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይት መድረኩ ላይ የሶማሌ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን ሀሺን ጨምሮ፣ የክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች፣ የሁለቱ ክልል ልዩ ኃይሎች ጠቅላይ አዛዦች፣ የመከላከያ አመራሮች እንዲሁም ከሶማሌ ክልል ፋፈንና ሲቲ ዞን ወረዳዎች፤ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች ተሳታፊ ነበሩ።

በምክክር መድረኩ ላይ የክልሎቹ ተጎራባች ወረዳዎች በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ እስካሁን የተሰሩ መልካም ሥራዎችን ከተመለከቱ በኋላ አልፎ አልፎ ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ መፍትሔዎች ላይ ያተኮሩ ሪፖርቶች አቅርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። ውይይቱ ከለውጡ በፊት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ሲከሰቱ የነበሩት የሕዝብ ግጭት እና ዜጎችን ወደ ግጭት እንዲገቡ የሚያደርጉ ችግሮችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ያለመ እንደሆነ የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ ቃሲም ገልፀዋል።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*