ሃይማኖ-ቲካ – ሙሉዓለም ገ.መድኀን

ፖለቲካዊ እስልምና እና መስመሮቹ

ከቅድመ-ዝግጅቱ እስከ ክንውኑ በቦታ ምርጫ ውዝግብ በታጀበው ሰሞነኛው የአዲስ አበባ የጎዳና ኢፍጣር፣ በመርሐ-ግብሩ ላይ ከተላለፉ መልዕክቶች ውስጥ ከእምነቱ ተከታዮች ውጭ ያሉትን ብዙሃን ተመልካቾች ግራ-ያጋባ አንድ ኹነት ተስተውሏል። የፍልስጤማውያንን ጉዳይ እንደ መሪ አጀንዳ ያደረጉ መልዕክቶች ይዘትና የፍልስጤም ባንዲራ ከፌዴራሉ እኩል ታይቷል። እያደገ በመጣ ብሔረተኝነት ውስጥ ሃይማኖታዊ መካረሮች ከመለንቀጣቸው አኳያ፣ ክስተቱን በስጋት ማየቱ ምክንያታዊ ይመስለኛል።

በዕለቱ “ፍልስጤም በልባችን ውስጥ ናት” ከሚለው ቀለል ያለ መልዕክት ጀምሮ “WE ARE ALL ONE UMMAH” የሚል መልዕክት ያስተላለፉ ወጣቶች፣ በፍልስጤም ባንዲራ ታጀበው በመስቀል ዐደባባይ ውለዋል። በዚህ ዐውድ፣ ይህንን ክስተት ከድንበር ተሻጋሪ የዲን (ሃይማኖታዊ) ትስስር ነጥሎ፣ በፖለቲካዊ እስልምና መነጽር ለማየት የሚያስገድዱ ማሳያዎችን እጠቅሳለሁ።

እዚህ ጋ ማስታወስ የምፈልገው በኢትዮጵያ እንኳንስ ዛሬ፤ ትላንት “ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ” የሚል የዘውድ መጠሪያ የነበራቸው ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ከፍልስጤም ጎን መቆማቸውን ነው። ከንጉሡ በኋላም፣ የተፈራረቁ ገዥዎች ውግናቸውን ለፍልስጤም ስለማድረጋቸው የታሪክ መዛግብት ያትታሉ። ሌሎች የኢትዮጵያ ግራ-ዘመምም ሆነ ተራማጅ የፖለቲካ ቡድኖች ከፍልስጤም ጎን መቆማቸውን ዓለም አይዘነጋውም።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*