ህይወትን ለማስቀጠል የተከፈለ መስዋትነት | በእስራኤል ጌታሁን

ዚህ ዐውድ ዛሬ የማስነብባችሁ ታሪክ ተረት አልያም የሆሊውድ ፊልም ሊመስል ቢችል አይገርምም። ግና እውነተኛ ታሪክ ነው።

የዛሬ 27 ዐመት፣ እ.ኤ.አ ኤፕሪል 7/1994 ሀሙስ ጠዋት ነው። ሁለት ሚሊዮን ፓኬጆችን ከከተማ ከተማ፣ ከአገር አገር በየቀኑ በፍጥነትና በቅልጥፍና ለደንበኞቹ የሚያደረሰው የአሜሪካው “fed-ex (federal express)” ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 705 MacDonald daggles DC-10-30F JHON PETER JUNIOUR የተባለው አውሮፕላን፣ ከአሜሪካዋ ሜምፕሲ ቴነሲ ሦስት የበረራ ባለሞያዎችን እና አንድ ተረኛ ያልሆነ የበረራ ኢንጂነር ባልደረባቸውን አሳፍሮ እዛው ወደምትገኘው ሳንሆሴ ካሊፎርኒያ ያኮበኩባል።

አብሯቸው እንዲበር የተፈቀደለት የበረራ ኢንጂኒየር ኡፈር ካሎዌ ወደ አውሮፕላኑ የገባው የጊታር ቦክሱን ይዞ ነበር። ረዳት አብራሪው ጂም ታከር ኡፈርን ሲያየው በመገረም፡-

“ጊታር ትጫወታለህ እንዴ?” ብሎ ጠይቀው፤

“አታውቅም እንዴ?! በደንብ እኮ ነው የምጫወተው፤” ሲል በፈገግታ መለስሎት ወደ አውሮፕላኑን ውስጥ መሰስ አለ። በልቡ ‹ታያለህ እንዴት እንደምጫወትብህ› ሳይለው አልቀረም። የህይወታችን ትልቁ ስህተት፣ አጠገባችን ያሉ ሰዎችን ሁኔታ በማጤን፣ ምን ሊያረጉ እንዳሰቡ ለማወቅ አለመሞከራችን ነው። ለምሳሌ እነዚህ የበረራ ባለሞያዎች የሰውነት እንቅስቃሴን ማንበብ ቢችሉ፣ ነገሩ እዛው ያበቃ ነበር። እኛም ዛሬ አጀንዳ ባላደርግናቸው ነበር። የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ሲዋሽ ዓይኑ ይጠባል፤ እጁ ወደ ፊቱ ይሄዳል። ከባሰ ደግሞ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*