
በተስፋና ደስታ የታ በው የ2010ሩ ለውጥ፣ የ“ብልፅግና”ን guillotine ከማዋለድ ባለፈ፤ የፈየደው ነገር፡- “አዲስ ራዕይ”ን፣ በ“ጌታ ራዕይ” መቀየሩ ነው። የአራቱ ዐመት ሰቆቃዎችም፣ ከአገሪቱ የቅርቡ ክፍለ ዘመን ታሪክ፣ የከፉ ናቸው። መንግሥታዊ መዋቅሩም፣ እንዲህ ተዳክሞና በሴራ ወይቦ የታየበት ጊዜ መኖሩን እንጃ?! በልጅ እያሱም ቢሆን። የችግሮቹ መነሾ ደግሞ፣ በወጉ ባልተቀበረው (ወይም እንዳይቀበር በተከላከለለት) ኢሕአዴግ ላይ ደርቦ መብቀሉ ነው። በአስረጂነት ሦስት ማሳያዎችን እጠቅሳለሁ። ቀዳሚው፣ የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፀጋ አራጋው ለድርጅቱ የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን፣ በግልባጫ ለሊቀ-መናብርቱ ያቀረበው ማመልከቻ ነው። ሁለተኛው፣ በማኀበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው የሥራ-አስፈጻሚ አባል ርስቱ ይርዳው ንግግር ሲሆን፤ ሦስተኛው፣ የሶማሌ ክልል ስንጥቃት ነው። በአናቱም፣ በኦሮሚያ፣ በዐማራ እና በሌሎቹ ቅርንጫፍ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ ግርድፍ መንፈራቀቆችን እያሰላሰላችሁ ተከተሉኝ።
የፀጋ መንገድ…
አቶ ፀጋ “ብልፅግና ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የሕግ ጥሰትና የአሠራር መዛነፍ እንዲስተካከል ስለመጠየቅ” በሚል ርዕስ፣ አስደንጋጭ ኬቶችንና ድርጅታዊ ቀውሶችን ቢያጋልጥም፤ እኒያ የታጨቁ እውነታዎች ግን፣ የኪሏቸውን ያህል በኩረ-ነገር አለመሆናቸው ያሳዝናል። ሕግና ተጠያቂነት ቢኖር፣ ደብዳቤው ላይ የሰፈሩት ወን ሎች ብቻቸውን፣ ፓርቲው ታግዶ ምርመራ እንዲደረግበት ባስገደዱ ነበር።
አሁን፣ ብልፅግና የዶ/ር ዐቢይ አህመድ የግል ኩባንያ እንደሆነ ያስረገጠበትን ኃይለ-ቃል እናብበው፡-
“የፓርቲው ፕሬዚዳንት፣ ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሆነውን የፓርቲ ተቋም የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብስባን በማጠፍና በመተው፣ በሕግም በአሠራርም በሞራልም የማይመለከታቸውን ኢ-መደበኛ አደረጃ ቶችን በመሰብሰብ፣ መደበኛ የሆነውን የፓርቲ ግንባታ ሥራ ወደ ጎን በመተው፣ ኔትዎርኩን አግባብ ባልሆነ ስምሪት በማጨናነቅ ‘ጊዜ የለም’ በሚል ሰበብ፣ ሕጋዊ የሆነውን የፓርቲውን የፖለቲካና የትግል መድረክ ሆን ብሎ የማቀጨጭ አቅጣጫን መከተል የፓርቲውን ቁመና በእጅጉ ጎድቶታል። […] በፓርቲው ውስጥ ዴሞክራሲያዊ አሠራር እየቀረ፣ በፀረ-ዴሞክራሲያዊ አሠራር እየተተካ፤ የጋራ ተሳትፏዊ አሠራር እየቀረ፣ በግለሰብ የግል ፍላጎትና በተናጠላዊ እንቅስቃሴ ሁሉም ነገር እየተሠራ፤ የግለሰብ ተንቀሳቃሽ ንብረት እስኪመስል ድረስ ተቋማዊ ህልውናውን እስከማጣት ሊያደርስ የሚያስችል የህልውና አደጋ ተደቅኖበታል። የፓርቲው ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በተቋማዊ አሠራር ሥርዐት ስትጠይቃቸው፣ ሁሉም በፓርቲ ደረጃ የሚሠራውን እንደማያውቁና መረጃ እንደሌላቸው ይነግሩናል።”
Be the first to comment