“ለአዲስ አበባ አይሆኑም!” | በተመስገን ደሳለኝ

ነገ በስቲያ የሚካሄደው ምርጫ፣ በጠቅላይ ሚንስትሩ አባባል የ“ጨበራ ምርጫ” ወደመምሰል አዘምሟል። የትግራዩ እንደተጠበቀ፤ የሶማሌ እና የሐረሪ ክልሎችም ለሦስተኛ ጊዜ ተራዝሟል። የኦሮሚያውም ለፎርማሊቲ ካልሆነ በቀር፤ ብልፅግና “ከጥላው ጋር የሚወዳደርበት” ነው። የዐማራ፣ የደቡብ፣ የቤንሻንጉል፣ የአፋርም ቢሆን “ግማሽ ጎፈሬ፣ ግማሽ ቢሊጮ” ነው።

በርግጥ፣ የችግሩ ስንክሳር ይሄ ብቻ አይደለም። ቦርዱ የማያውቃቸው 79 የ“ጨረቃ ምርጫ ጣቢያዎች” ስለመገኘታቸው ተዘግቧል። ይህ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደራዊ መዋቅር፣ እንደ ፈንድሻ በየመንደሩ የተበተኑት የኮሚኒቲ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ብሔራዊ ደህንነትና የመሳሰሉት ተቋማት በጥልቅ እንቅልፍ ተውጠዋል። ጎዳና ላይ የተተከሉ ጥቂት አበባዎች ስለመሰረቃቸው ፈጣን መረጃ የሚደርሳቸው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድም ‘የሚያውቁት ነገር የለም’ ተብሏል።

እኒህ ክስተቶች፣ በተስፋና በደስታ የተጀመረው ምርጫ፣ በቀቢጸ-ተስፋ እና በሀዘን እንዲቋጭ መጥፎ ምልኪ ቢሆኑ አይገርምም።

የሚገርመው፡- የአፍሪካ መዲና፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች መቀመጫና አያሌ ኃላፊነቶችን የደራረበችው አዲስ አበባ፣ በአንድ ብሔር ባለ-ቤትነት ወደመዋጥ መገፋቷ ነው። ባለፉት ሦስት ዐመት የኦሮሚያ ብልፅግና በመንግሥታዊ መዋቅር ተከልሎ የፈጸመባት ልቅ-ሴራ አደክርቷታል። 48 ሰዓት ብቻ የቀረው ምርጫ ደግሞ፣ የመጨረሻው ሚስማር የሚመታባት፤ አልያም ወገግታ የሚፈነጥቅባት ነው።

ሰሞኑን በማኀበራዊ ሚዲያ “ለአዲስ አበባ አይሆኑም” በሚል ሃሽታግ ሲዘዋወር የነበረው ሃሳብ፣ ለዚህ ተጠየቅ ርዕስ መደረጉን አስታውሰን፤ አዲስ አበባን ማን ይታደጋት? የሚለውን ጥያቄ እያሰላሰልን፣ የ“አባ ኮዳ” ፖለቲካን በጨረፍታ እንቃኛለን።

ሕገወጡ ማነው?

ስለ-አዲስ አበባ ስንነጋገር ከኦሮሚያ እና ዐማራ የባለቤትነት ጥያቄዎች ጋር መፋጠጣችን ተገማች ነው። የሁለቱም ፍላጎት ሕገ-ወጥ ቢሆንም-ቅሉ፤ የኦሮሚያው ወደ ወረራ ተቀይሯል። “እንደ ዐይናችን ብሌን እንጠብቀዋለን!” እየተባለ የሚፎከርለት ሕገ- መንግሥት ተገርስሶ፣ አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” የማድረጉ ፕሮጀከት ተፈጣጥኗል፤ (በዚህ ዙሪያ ከተሰናዱ ጥናታዊ መድብሎች ግዘፍ-የሚነሳ አበርክቶ ያለው በአምላኩ ኃ. ስዩም “የአዲስ አበባ ጉዳይ፡- ታሪካዊ፣ ሕገ-መንግሥታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ” በሚል ርዕስ በ2011 ዓ.ም ለንባብ ያበቃው ነው። ለዚህ ጽሑፍ ማጠናከሪያ አብዝቼ መኮረጄን ቀድሜ ገልጫለሁ።)

የሕገ-መንግሥቱ “ትርፍ አንጀት” ተደርጎ የሚቆጠረውን የ“ልዩ ጥቅም” መብት፣ በመለጠጥና ከዐውዱ በመነጠል መቀመጫውን ሸገር የደለደለው የኦሮሚያ ክልል፣ የከተማዋን የራስ-ገዝ አስተዳደር በዐደባባይ ንዷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ፣ የ“ልዩ ጥቅም” ጥያቄውን ወደ ባለቤትነት መብት አሳድጎታል። ይህ ድርጊት፣ ሕገ- መንግሥቱንም ሆነ የአዲስ አበባ መተዳደሪያ ቻርተርን በግላጭ የደፈጠጠ መሆኑን በዚህ ጽሑፍ እናጠይቃለን።

“ክልል 14”  ….

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*