ሕወሓትን ከማስወገድ ሌላ አማራጭ አልታየኝም! | ግርማ ሰይፉ ማሩ

ባለፈው ጽሑፌ “ሕወሓት መደምሰስ አለበት!” የሚል መደምደሚያ ላይ ያደረሰኝን የድርጅቱን ሠነድ በአጭሩ አጋርቻችሁ እንደነበረ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ፣ ሠነዱ በእርግጥም የእነርሱ መሆኑን በምልዓት እንድናምን የሚያደርገን “በተጋሮዎች ዘንድ በምስጢር ሲዘዋወር ነበር” የተባለለት በትግርኛ የተሰናዳ ሠነድ መውጥቷ ነው። እንዲህ ይላል፡-

“…የአንድ ሕዝብ ስትራቴጂካዊ አካሄድ የሚተነብይ፣ የትግል ሰነድ የያዘ፣ በጠላት እጅ ገብቶ ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ። በዚህ ጉዳይ ጥልቅ ግምገማ ተካሄዶ ለቀጣይ አንድ የመከላከል አቅጣጫ መከተል ይኖርብናል።”

ሠነዱ “በጣላት እጅ ገባ” ያሉት፣ እኛ በማየታቸን ሲሆን፤ “ችግር ተፈጠረ” የተባለው ደግሞ ‹ሕወሓት መደምሰስ አለበት› ብለን አቋም መያዛቸን ነው። መቼም ከዚህ በኋላ የድርጅቱ ደጋፊዎች “እነ እገሌ ጽፈው ነው ያሰራጩት!” የሚሉትን ማስተባበያ፣ ከዚህ በኋላ እርማችሁን አውጥው ይተዉቷል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ምክንያቱም “የትግራይ ተቆርቋሪ ነን” የሚሉት መሪዎቻቸ ባወጡት ሠነድ ያረጋገጡልንን፣ የቀደመውም ሠነድ የእነርሱ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ ዜጎች ልንነቃና የአገር ህልውና ተዘናግተን አደጋ ላይ እንዳንጥል የማያስጠንቅቅ ነው። ስለዚህም ብቸኛው መፍትሔው ሕወሓትን መገላገል ነው።

ይህ በትግርኛ ተዘጋጅቶ፣ በተጋሮዎች ዘንድ በምስጢር የሚዞረው ሠነድ፣ አሁንም ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ ከዚህ የከፋ ስቃይ ሳያዘንብ እንደማይላቀቅ ያሳረግጣል። በጥቂቱም ቢሆን፣ በትግራይ ፓርቲዎችም ሆነ በፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራሩ መካከል መከፋፈል መኖሩንም ይጠቁማል። በትግራይ ውስጥ፣ በተቃዋሚ ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፓርቲዎች፣ በኋላ ሕወሓትን ተከትለው ወደ ቆላ ተንቤን መሸሸጊያ ቦታዎች አብረው ቢወርዱም፤ መተማመን ያቀታቸው መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል። “የውስጥ ችግራችንን ፈተን፣ ጠላቶቻችንን እንመክት” የሚል ጥሪም ያቀርባል።

 Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*