መጅሊሱን በ“ምርጫ”፣ ሥልጣኑን በቅርጫ! | ጁሃር ሳዲቅ (ጋዜጠኛ)

ዚህ ርዕስ ሃሳቤን እንዳካፍል የገፋፋኝ የፖለቲካል ኢስላም ርዕዮተ-ዓለም አቀንቃኞች፣ መጅሊሱን በምርጫ ሰበብ ለመጣል የሚጎነጉኑት ሴራ ነው። ወሃቢዝም፣ ሙስሊም ብራዘር-ሆዶች፣ ፖለቲካል-ኢስላም… አራማጆች የኢትዮጵያን መሬት ከረገጡ ጊዜ ጀምሮ፣ መጅሊሱን ቅርጫ ለማድረግ እንደ ቀጥር እባብ የመክለፍለፋቸው አባዜ ዛሬም ተግ ሳይል መቀጠሉን የታዘበ፣ ባልተገራው የሥልጣን ጥማታቸው መደንገጡ አይቀርም። በጣም የሚገርመው ደግሞ ‹ምርጫ፣ ምርጫ…› እያሉ የሚላዝኑት፣ ለዴሞክራሲ ካላቸው ቀናኢነት አስመስለው ለመሸወድ የሚጋጋጡት ነገር ነው። እጅግ ኋላቀርና ቀንደኛ ፀረ-ዴሞክራሲ መሆናቸውን፣ ከ97ቱ እስከ 6ኛው አገር ዐቀፍ ምርጫ በበቂ ለመታዘባችን፣ እኛው ራሳችን ህያው መስክር ነን።

እኒህ ጠርዝኛ አድሃሪያን (Opportunist) ኢሕአዴግ የሃይማኖት ፖሊሲው ላይ ነፃነት መፍቀዱን ተከትሎ፣ የኢክዋን እና የወሃቢዝም ዓላማቸውን ለማስፈፀም Populistነትን አለቅጥ አጎነውና መጅሊሱን በፖለቲካ ሴራ ጠልፈው፤ ነባር ሙስሊሞች ለዘመናት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለው ያቆመትን ተቋም ሥልጣን ለመቀራጥ መራሯጥ የጀመሩት ገና አምስት ዐመት እንኳ ሳይሞላው እንደነበረ ይታወሳል። መጅሊሱን እና መስጂዶችን የብጥብጥና ሁከት ማዕከል ለማድረግም ጊዜ አልፈጀባቸውም።

በዋንኛነት በፓን-ዐረቢዝም ርዕዮተ-ዓለም የተጠመቁት እነዚህ ሰዎች፣ በመጅሊሱ ግንባታ ሂደት ላይ አንዳችም አስተዋጽኦ ሳይኖራቸው፤ በዚህ ላይ መጅሊሱ የሃይማኖት እንጂ፣ የፖለቲካ ተቋም አለመሆኑን እያወቁ፤ የሳዑዲ እና የግብፅን ፖለቲካ ለማራገፍ ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልባጠጡት ሸንተረር የለም።

በዚህ እብሪት በሞላው ድርጊታቸው፣ የኢልም (የመንፈሳዊ ትምህርት) ማዕከል መሆን የሚገባቸውን መስጂዶች፣ የልዩነት መስበኪያና የፖለቲካ ፓርቲ ቢሮ እስኪመስሉ በፅንፍኛ አስተሳሰቦች እንዲወጠሩ አድርገዋል። ከሃይማኖት ወጥቶ ፅንፈኛ የሳዑዲ ወታደር አዛዥ እና ብሔርተኛ (commander and national­ist) የሆነውን የአብዱልወሃብ የፖለቲካ አስተሳሰብን በመጫን፣ ህፃናትን ከሞራል እሴቶች በማራቅ፣ ትላልቅ የሃይማኖት አባቶች (ኡለማእ/መሻይኽ) እንዲናቁ በማድረግ፣ ተቋሙ መሪ እና ክብር አልባ እንዲሆን ያደረጉት ጥረት ፍሬ ወደ ማፍራቱ ማዘንበሉ ሁላችንንም ሊያስቆጨን ይገባል።

Continue reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*