
የጦርነት አዘጋገብ እና አጻጻፍ የራሱ የሆነ ቅደም- ተከተል ይኖረው ይሆናል። እኔ ይህንን ስጽፍ እሱን አልተከተልኩም። በቦታው ሆኜ ያየሁትን እና ከግንባር የተመለሱ የመከላከያ፣ የዐማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላትን በማነጋገር ነው።
ከመቀሌ ልጀምር…
መከለከያ እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትግራይን ለቀው ሲወጡ፣ መረጃው ያልነበራቸው የሠራዊቱ አባላት እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ የበታች አመራሮች በሕወሓት ታጣቂዎች እጅ ወድቀዋል። ከመቀሌ 11 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ኩኻ የጦር ሰፈር ሲሰለጥኑ የነበሩ ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ ፖሊሶችም እንዲሁ መረጃው ስላልነበራቸው፣ የተወሰኑትን ታጣቂው ተቆጣጥሯቸዋል። ጥቂቶቹ ወደ መሃል አገር ሲገቡ፤ አብዛኛዎቹ ወደ ኤርትራ ተሰደዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በአክሱም፣ በአዲግራት እና በመቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ወደ አራት ሺሕ የሚጠጉ ተማሪዎችም ጉዳይ ተዘንግቶ ነበር።
ከትግራይ የወጣው የመከላከያ ሠራዊት ከራያ ቆቦ አቅራቢያ ጮቢ በር እስከ ወልዲያ ባለው መስመር ለተወሰኑ ሳምንታት ያህል ሰፍሮ ሰንብቷል። የዐማራ ልዩ ኃይል እና ከክልሉ የተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ የሚሊሻ አባላት ደግሞ፣ ቀደም ሲል ይዘውት የነበረውን ኮረምን እና በኮረም ዙርያ የሚገኘውን የኦፍላ ወረዳን ጨምሮ፤ አላማጣን እስከ ባላ ድረስ ያለውን ሜዳማ አካባቢ አጠናክረው ይዘው ቆይተዋል።
በራያ አላማጣ ባላ በኩል የነበረው የሚሊሻ ኃይል አብዛኛው “ለስልጠና ትፈለጋላችሁ” በሚል፣ አንዳንዶቹ ጋቢያቸውን እንደደረቡ፣ የተቀሩትም የሥራ ልብሳቸውን እንደለበሱ ከእርሻ ሥራቸው ላይ ተጠርተው ነው ወደ ግንባር የተላኩት። አስቀድመው ወደ ስፍራው የደረሱ ሚሊሻዎች ከቤተሰብ እየደወሉ ገንዘብ በማስላክ ከአካባቢው ጋር የሚስማማ አልባሳት እና የሚያስፈልጋቸውን ያሟሉት ግንባር ከደረሱ በኋላ መሆኑንም ሰምቻለሁ።
ሐምሌ 4 ምሽት ከየዞኑ የተውጣጣው የሚሊሻ ኃይል “ባላ ባንድራ” ወደሚባለው አካባቢ ተጠቃልሎ ገብቷል። ሐምሌ 5 ከማለዳው 12፡00 ላይ ለወታደራዊ ልምምድ› ወደሚያደርጉበት ቦታ ለመሄድ መንገድ ሲጀምሩ የተፈጠረውን ክስተት በወቅቱ ከሚሊሻዎቹ አንዱ የነበረው ሞላ ጌታሁን ያስታውሰዋል። “ከወደ ተቃራኒው አቅጣጫ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ተተኮሰብን።” ….
Be the first to comment