ስለ ተጋሩ እጮኻለሁ! – በፍቃዱ ኃይሉ

የትግራዩ ጦርነት ከተጀመረ አራት ወራት ከግማሽ አለፈው። ስለ ቅድመ ጦርነቱ ሁኔታ፣ ስለ ጦርነቱ ጀማሪ፣ ስለ ድኅረ-ጦርነቱ ቀውስ ተጠያቂ ማንነት ብዙ አካራካሪ መረጃዎች ተነግረዋል፤ እየተነገሩም ነው። ጦርነቱ በተካሄደበት ሜዳ፣ ትግራይ ክልል ውስጥ የፍዳው ገፈት ቀማሽ ስለሆኑት ብዙሃን እና በምኑም የሌሉበት የትግራይ ተወላጆች (ብዙሃን ተጋሩ) ግን፣ በበቂ ሁኔታ አልተነገረም። የድረሱላቸው ጩኸት፣ በበቂ አልተጮኸም።

ኢትዮጵያውያን በታሪካችን ደግመን ደጋግመን ከምንሠራቸው ስህተቶች ውስጥ ለገዢዎች ጥቅም እንደ ሕዝብ የሚያስተሳስሩንን ድልድዮች ሰብረን አጥር ካቆምን በኋላ፣ መልሰን መፀፀታችን አንዱና ዋነኛው ነው። ዛሬም በሥልጣን ድልድል እና ርስት ጉዳዮች የብዕር ሥም የተሸፈነው የገዢዎች ጭካኔ የተሞላበት ሽኩቻ የዜጎቻችንን እልቂት፣ መታረዝና መዋረድ አስከትሏል። ይህ ግፍና መከራ ከዐመት ዐመት አፈር ለሚገፉ ገበሬዎቻችን ምንም ሳያተርፍ ማለፉ አይቀርም።

ከዘመናት በኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው ‘ለዚህ ነው ከወገኖቼ የተቆራረጥኩት’ ብለን ለምንፀፀትበት የዝሆኖች ፀብ ሰበብ አስባብ ከመታለላችን በፊት፣ ስለ ሳሩም እንናገርለት።

ዘገባዎቹ ምን ይላሉ?

ላለፉት ዐመታት፣ በየዐመቱ የሚደረገው የጉዞ ዐደዋ ዘንድሮ ከተጀመረ በኋላ ተቋርጧል። ከጉዞው አዘጋጆች መካከል ያሬድ ሹመቴ ‘መንገዱ የደኀንነት ሥጋት ስላለበት፣ ይቅርባችሁ ተብለን ነው ያቋረጥነው’ ብሎ ለሚዲያ ተናግሯል። ምናልባትም፣ ጥበቃ ሊያገኙ የሚችሉ እነዚህ ከተሜዎች ‘መንገዱ አደጋ ነው’ ተብለው ከመጓዝ የቀሩበት አገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች አሉ።

Continue Reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*