ትግራይ የተለቀቀችበት ቁማርና እንደምታው! | እስክንድር ነጋ (የህሊና እስረኛ ቂሊንጦ፣ አዲስ አበባ)

ለ5 ዐመት ተመርጦ ሲያበቃ፣ ኮቪድ-19ን ታክኮ አንድ የሥልጣን ዐመት ለራሱ የጨመረው ፓርላማ፣ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም የመጨረሻውን ስብሰባ አድርጓል። በዕለቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው የመጀመሪያ ክፍል በተለያዩ ጉዳዮች ገለፃ ከሰጡ በኋላ፤ ከሻይ እረፍት ሲመለሱ ሁሉም በጉጉት በጠበቀው የትግራይ ጉዳይ ላይ ሰፋ ላለ ጊዜ ተናግረዋል።

በቅደም ተከተል ባያስቀምጡትም፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ በሦስት የተከፈለ ነበር። አንደኛው፣ በሕወሓት በኩል ተፈጽመዋል ያሏቸውን የፖለቲካ ህፀፆች (በእሳቸው አባባል “miscalculation”) የዘረዘሩበት ነው።

ሁለተኛው፣ ጦሩ ትግራይን የለቀቀው በሽንፈት ነው ወይ? በሚል በምክር ቤቱም ሆነ ከምክር ቤቱ ውጭ ሲብላላ ለነበረው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ “የአወጣጡ ሂደት ነበር” ያሉትን በሦስት ምዕራፎች ከፋፍለው የተረኩበት ነው።

ሦስተኛው፣ ጦሩ ከትግራይ እንዲወጣ ለምን እንደተወሰነ የገለጹበት ነው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሕወሓት በኩል እስካሁን ተፈፅመዋል ያሏቸው ትላልቅ ህፀፆች ሁለት ናቸው። ሦስቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ቁርኝታቸውን ከግንባር ወደ ውህድ ድርጅት ሲያሳድጉ፣ የግንባሩ መሥራች የነበረው ሕወሓት አሻፈረኝ ማለቱ የመጀመሪያው ስትራቴጂካዊ ህፀፁ ነው። የብልፅግና አባል ቢሆን ኖሮ፣ ቢያንስ በፌዴራልም በክልልም ደረጃ የነበረውን ይዞ መቀጠል ይችል እንደነበረ ተናግረዋል። በዚህ አማራጭ ላይ ተረማምዶ ወደ ትግራይ ካፈገፈገ በኋላም፤ በክልሉ ተገድቦ በሰላም ቢኖር ኖሮ፣ “በእኛ በኩል የጦርነት ፍላጎት አልነበረም፤ ማንም አይነካውም ነበር፤” ብለዋል። ሆኖም፣ ሁለተኛው ህፀፁን በመፈፀም፣ በመሃል አገር ብጥብጥ ለመቀስቀስ ከመሞከሩ ባሻገር፤ ማዕከሉ መቀሌ የነበረውን የሰሜን ዕዝ አጥቅቶ፣ የአገሪቱን 80 ከመቶ የጦር መሳሪያ በእጁ ማስገባቱን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የህፀፁን ነገር በዚህ አላቆሙም። ቀጠል አድርገው ‘ሕወሓት በቀጣይነት ሊፈፅም ይችላል’ ያሉትን ህፀፅ በምሳሌ ሲያቀርቡ የእስራኤል ታሪክን አንስተዋል። ‘ሕወሓት ተከዜን ተሻግሮ ወደፊት ለመግፋት የሚሞክር ከሆነ፤ እስራኤላዊያን ግብፅን ለቀው ሲወጡ፣ ከመንገድ እንዲመልሳቸው ተልኮ በወጣበት እንደቀረው የፈርኦን ጦር ይሆናል፤’ ብለዋል።

1.2. የጦሩ አወጣጥ ከትግራይ

ጠቅላይ ሚንስትሩ “ጦሩ ከትግራይ የወጣበት ሂደት” ብለው በሰጡት ማብራሪያ፣ ለአድማጮቻቸው ዐዳዲስ መረጃዎችን አካፍለዋል። …..

 Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*