አሜሪካ ያልተመቻት ምንድነው? | ክፍሉ ታደሰ

ኔ 21/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማድረግ፣ በድንገት ከመቀሌና ከዋና ዋና የትግራይ ከተሞች ለቆ ወጣ። ይህ ድንገተኛ እርምጃ አንዳንድ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች የሚኖሩት ቢሆንም፤ ውሳኔው የኢትዮጵያ ሕዝብን አስደነገጠ። ሕወሓትና ደጋፊዎቹ በወሰዷቸው እርምጃዎች፣ አንዳንድ ‹የመንግሥት ደጋፊ› ተብለው በሚቆጠሩ ወገኖች ላይ ጉዳት ደረሰ። በተለያዩ የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ የሆኑ ወጣቶች ለአደጋ ተጋለጡ።

መንግሥት የወሰደውን ይህን እርምጃ ሕወሓት አልተቀበለውም። እንዲያውም መሳለቂያ አደረገው። የምዕራብ አገራት መንግሥታትም ጦርነቱ እንዲቆም ሲወተውቱ የቆዩ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደው እርምጃን ብዙዎቹ በዝምታ ለማለፍ ወሰኑ። ከሰኔ 21 በኋላ በነበረው ጊዜ የሕወሓት ኃይሎች ያካሂዱ የነበሩትን መጠነ-ሰፊ ግድያ፣ ትንኮሳ፣ አፈና፣ የስደተኛ ጣቢያዎች ወረራ… ወዘተ ባላየ፣ ባልሰማ አለፉት። ከእነ አካቴው፣ የሕወሓት ኃይል፣ የዐማራ ክልልን ሲወር፣ ቡድኑ “እንዲታቀብ” በመገሰጽ ፈንታ፣ የሚያበረታታ መግለጫ ሰጡ። ይባስ ብለው፣ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል በመሰናዳት ላይ ናቸው። ዋና ዋና የምዕራቡ ዓለም ሚድያዎችም፣ ሙያዊ ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በመዘንጋት የሃሰትና ለአንድ ወገን ያጋደሉ ዜናዎች ሲያስተላልፉ ከረሙ። አሁንም እያስተላለፉ ነው። ይህ የሚድያዎቹም ሆነ የምዕራቡ አገራት አካሄድ፣ ሕወሓት በጥቅምት ወር የሰሜን ዕዝ ላይ መጠነ-ሰፊ እርምጃ ከወሰደ ጊዜ ጀምሮ ሲስተዋል የነበረ ሲሆን፤ ‹የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ› የሚለው የምዕራቡ ዓለም፣ ለዚህ ከባድ የሽብር እርምጃ አንድም ተቃውሞ አላሰማም። በማይካድራ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ሲጨፈጨፉም ምንም አልተነፈሰም።

ሰኔ 21 ቀን መንግሥት ተኩስ በማቆሙ፣ ትግራይ ውስጥ ገጥመውት የነበሩትን የተለያዩ ችግሮች ከጫንቃው ላይ አነሳ። ኳሱንም ወደ ሕወሓት ሜዳ ወረወረ። የፖለቲካ አካሄዱ የገባው የምዕራቡ ዓለምም ሆነ ሕወሓት ተደናገሩ። የምዕራቡ ዓለም ክሱን አላቋረጠም፤ ሕወሓትም ‹ጦርነቱን ቀጥላለሁ› አለ። ይህ ሁኔታ፣ የችግሩ ስረ-መሰረት ከትግራይ መውጣት- አለመውጣት፣ ጦርነት ማቆም ወይም አለማቆም ጋር የተያያዘ ሳይሆን፣ ከዚያ የዘለለ መሆኑን አመላከተ። ብዙዎቻችን ልብ አላልነውም እንጂ፤ ለ6ተኛው ዙር ምርጫ ዝግጅት ይደረግ በነበረበት ወቅት፣ የምዕራቡ ዓለም ‹ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ስለማይችል፣ በዚያ ፈንታ የብሔራዊ እርቅ መደረግ አለበት› ሲል ነበር፣ ሰሚ ባያገኝም። 40 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ፣ ብርዱንና ዝናቡን ተቋቁሞ ድምጹንና ፍላጎቱን ገለጸ። ከምርጫው ሰላምን መሻቱን አሳወቀ።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*