አንካሴው ምርጫ … – ዶ/ር ሔሮን ገዛኽኝ

ርጫ፣ ዜጎች ‹ለሕዝባዊ ኃላፊነት ይበጃል› የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ (ግለሰብ) የሚመርጡበት ወይም ‹አይሆነኝም› ያሉትን በድምጽ የሚሽሩበት ዴሞክራሲያዊ ሂደት ነው። ምቹ የፉክክር ሜዳ እና ብርቱ ተፎካካሪ አካላት የእውነተኛ ምርጫ አበይት ቁም ነገሮች (substance of elections) ተደርገው ይወሰዳሉ።

የምርጫ ጽንሰ-ሃሳብ ጅማሮን ከጥንት የአቴንስ እና ሮም የጳጳሳት እና ንጉሠ-ነገሥታት አቀባብ ጋር የሚያያይዙት ባይጠፉም፤ የዛሬውን ዐይነት መልክ ያለው የምርጫ ሂደት ግን ከ17ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ እንደተጀመረ ይነገራል። ምንም እንኳ፣ ዛሬ ምዕራባውያኑ ነፃ እና ተዓማኒ ምርጫን ከማከናወን አንጻር፣ እምብዛም ባይታሙም፤ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ፣ ምርጫዎቻቸው የአሜሪካ እና ፈረንሳይ አብዮቶች ያወጁትን የዜጎችን እኩልነት መርህ በመጣስ፣ የሴቶችን ነፃ ተሳትፎ ከመገደብ አንስቶ በበርካታ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ክንውኖች የታጀቡ እንደነበር የታሪክ ማህደራት ያስረግጣሉ።

ዛሬ ዴሞክራሲን ‹በሚገባ ታጣጥማለች› ተብላ የምትወደሰው ስዊዘርላንድ ሳትቀር፤ የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ በሕግ ማረጋገጥ የቻለችው በ1971 እንደነበር ይታወቃል። ታላቋ ብሪታኒያ በ1928፣ ፈረሳይ በ1944፣ ቤልጂየም በ1949 የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ መብት በሕግ ደንግገዋል። በርግጥ አገራቱ የሴቶችን በነፃነት የመምረጥ መብት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ቢደነግጉም፤ ቀላል ቁጥር የሌላቸው አባ-ወራዎች ለብዙ ዐሥርታት ሚስቶቻቸው እና ለዐቅመ ምርጫ የደረሱ ሴት ልጆቻቸው ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ሲወስኑላቸው እንደነበርም ታሪክ ያወሳል።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*