“አይሜሪካ” | ዋጋዬ ለገሰ

2003 ባግዳድ፤ ፍርዶስ አደባባይ ላይ የቆመው ግዙፉ የሳዳም ሁሴን ሃውልት ሲፈርስ ያልታየበት ቴሌቪዥን አልነበረም። ኢራቃውያን ከብበው እየጨፈሩ፤ በአሜሪካ ባንዲራ አይኑ የተጋረደውን ግዙፍ ሀውልት ሲገረስሱት የሚያሳየውን ዜና የአለም ሚዲያዎች ተቀባበሉት። ከሁሉም አፍራሾች መካከል ግን አል ጃቡሪ ዝነኛ ሆነ። ስፖርተኛውና በክብደት ማንሳት ውድደር ለሃገሩ በርካታ ሽልማቶችን ያስገኘው ይህ ኢራቃዊ፤ የአሜሪካ ወታደሮች ባግዳድ ገብተው ሃውልቱን ሲከብቡት ህልሙ እውን ሆነ። በፓክ አውት መዶሻውን ይዞ ወጣ በፈርጣማ ክንዶቹ ይነድለው ጀመር። ትእይንቱ በበርካታ ቴሌቭዥኖች ለእይታ በቅቶአል። የዚያን ጡንቻማ ሰው እልህ፤ እርካታና ወኔ ለኢራቃውያን ጸረ ሳዳም ሁሴናዊ ትግል ማሳያ አድርገው ተረኩት። Kadhim Sharif al-Jabouri በወገረው ሃውልት ውስጥ የሳዳምን አገዛዝ ሲገረሰስ መስለው አቀረቡት። “አዲስ ጸሃይ ወጣች አምባገነኑም ሄደ” አሉ። ነገሩ “አሜሪካ የነካችው ሆነና” እንደታሰበው አልሆነም። ኢራቃውያን በአሜሪካ በነተወረሩ ማግስቶች የመከራ ድርሳናቸውን መግለጥ ጀመሩ። 200 ሰው በኢድ ዋዜማ በመገበያያ ስፍራ በቦምብ አለቀ። ‘ሰሜናዊውን የሃገሪቱን ከፍል አይኤስአይኤስ ያዘው’ ተባለ። ኢራቃውያን በሚሊዮን እየተተቆጠሩ በስደተኝነት በየሃገሩ ፈሰሱ።

ጡንቺስቱ አልጃቡሪ፤ ሃውልቱን በገረሰሰ በ13ኛ አመቱ፤ የ60 አመት አዛውንት ሆነ። ባግዳድን ከለቀቀ ቆየ። ቤይሩት ከአንድ ሚሊዮን ስደተኞች ጋር በካምፕ ይኖራል።

ቢቢሲዎች አናገሩት። እንዲህም አለ፤ “ሃውልቱ በነበረበት ሳልፍ፤ ህመምና እፍረት ይሰማኛል። ለምን ያንን ሃውልት አፈረስኩት እላለሁ ለራሴ።ብችል መልሼ ብሰራው ደስ ይለኛል። ቡሽና ብሌይርን ባገኛቸው በባዲ እጄ እገድላቸው ነበር። ውሸታሞችና አታላዮች ናቸው”

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*