ኢትዮጵያ ወዴት…?

ሳይንሳዊ የፖለቲካ ትንተና ያላመቸችውን ኢትዮጵያ፣ የነገ ዕጣ-ፈንታ ‹ይህ ነው› ብሎ ለመናገር ቀርቶ፤ ለቢሆን ዕድል ትንበያ እንኳ አዳግቷል። በተለይም፡- የሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ የማስከበር ተልዕኮ አለመጠናቀቅ እና ድንበር ተሻጋሪነቱ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ኃይል የሚያደርሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አለመቆም፣ የሱዳን ሉዓላዊነትን መዳፈር፣ የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተከትሎ የውጭ ጫና ሙከራዎች ማየል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖር፣ መቆሚያ ያጣው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት፣ ማኀበራዊ ቀውሱ እና የሥራ-አጡ ቁጥር መበራከትንም ከወጣት ንረት (youth bulge) ጋር ደምረን ስንመለከተው፣ ‹ኢትዮጵያ ወዴት› የሚለው ጥያቄ በመለኮታዊ ምላሽ እንጂ፤ በሰዋዊ ስሌት የሚሆን አይመስልም።

እኒህ ክስተቶች ከድርጅት በላይ የገዘፉ በመሆናቸው፣ በዚህ ጽሑፍ አገርን ለማስቀጠል የሚረዱ ሃሳቦችን በወፍ በረር እንቃኛለን። የፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ ወድቀት መነሻዎችንም ጨርፈን እንመለከታለን።

ዛሬም የአውራ ፓርቲ ጉዞ

ሕወሓት/ኢሕአዴግ አራት ኪሎን ከረገጠ ጀምሮ በአስመሳይ (facade) የመድበለ ፓርቲ ሥርዐት ተንጠላጥሎ፣ ሥልጣንን በብቸኝነት ወደ መጠቅለል እብሪት በመቀየሩ፤ ፓርላሜንታዊ የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታን የማይቻል ዳገት (Uphill Stride) አድርጎት ቆይቷል። በዚህም በኢትዮጵያ ትልቁ የፖለቲካ ተቋም የሆነው ፓርላማ፣ የመጥፎ ገጽታ ምልክት መስሎ እንዲሳል አስገድዶታል። በተለየ ሁኔታ ከምርጫ 2002 ዓ.ም ወዲህ በተከታታይ በተመሰረቱት ምክር ቤቶች፣ የዴሞክራሲ ሥርዐት የግድ የሚለውን የፖለቲካ ብዝሃነት ጨርሶ እንዳይታይም አጨልሞታል። እነዚህ ሂደቶች ‹ኢሕአዴግን ወደ አውራ ፓርቲነት ያመጡ› ተብለው መጠቀሳቸው እውነት ነው። በርግጥ ውድቀቱንም አፋጥነውታል።

አጥኝዎች እንደሚሉትም ተከታታይ ምርጫዎችን የማሸነፍ እርከን (threshold)፣ ገዥ ፓርቲዎች (በሕግም ሆነ በአሠራር) ኢ-ፍትሐዊነት የምርጫ ውጤቶችን በብቸኝነት እንዲቆጣጠሩና በፖለቲካዊ ማንአህሎኝነት እንዲወጠሩ ያደርጋቸዋል። ይህ ስሜት፣ የአውራ ፓርቲው አባላት ፓርላማው የእነሱን ፍላጎትና ጥቅም ከማስከበር በዘለለ፤ ዴሞክራሲያዊ አበርክቶ እንዳይኖረው ያግደዋል። በድምር ውጤቱም ሕግ አውጪው፣ ሕግ አስፈጻሚውን የሚቆጣጠርበት ዕድልን ስለሚያጠብ ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲን ይቀብራል። ከክትትልና ቁጥጥር ውጭ የሆነ አስፈጻሚ አካል ደግሞ፣ አገርን እንዴት ወደ መቀመቅ ሊከት እንደሚችል ከእኛዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ማሳያ የለም። ….

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*