ኢትዮጵያ ዳግማዊ አብዮት ያስፈልጋታል! ጊዜው ደግሞ አሁን ነው! | ኃይሉ አርአያ (ዶ/ር)

የካቲት 1966 ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀዳማዊ አብዮትን አካሄደ። በዚህ አብዮት ለዘመናት ስር ሰድዶ የኖረውን የፊውዳል ሥርዐት አስወገደ። በአሁኑ ጊዜ የግዴታ ዳግማዊ አብዮት ማካሄድ አስፈላጊ ሆኗል። ዳግማዊ አብዮቱ “የዕውቀት እና የእሴት አብዮት” ነው። የአገራችን ኋላቀርነት ለዘመናት የቆየ፣ ሥር የሰደደና የተጠራቀመ በመሆኑ፤ መቀሰም ያለበት የሳይንስ እና ተክኖሎጂ ዕውቀትም እጅግ ሰፊና በፍጥነት ተለዋዋጭ በመሆኑ፣ በመደበኛ አሠራር እና በመደበኛ ጊዜ የሚጠበቀውን ለውጥ ለማምጣት አይቻልም። ስለዚህ፣ የለውጡ ሂደት የግዴታ አብዮታዊ መሆን አለበት።

አብዮቱ ጣምራ ግብ አለ ው።

አንደኛው ግብ፡- ከላይ እንደተባለው፣ ዘመናዊ ዕውቀትን፣ በተለይም ሳይንስ እና ተክኖሎጂን፣ በአብዮታዊ ፍጥነትና በጥራት መቅሰምና ሥራ ላይ ማዋል ነው።

ሁለተኛው ግብ፡- ለዘመናት ተፈትነው ጠቃሚነታቸው የታወቀ ማኀበራዊ እሴቶች፣ ለምሳሌ ነፃነት፣ እኩልነት፣ መከባበር፣ መተባበር፣ ፍትሕ፣ መተሳሰብ … ይበልጥ ዳብረውና ተከብረው፣ የሳይንስ እና ተክኖሎጂ ውጤቶች ሥራ ላይ ሲውሉ፣ ሳይታሰብ የሚያስከትሏቸው ጉዳቶችን በጥሞና በመታዘብና ማስተካከያ ምክሮችን በመስጠት ጠቃሚ ኃይል ሆነው እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው። ለምሳሌ ፋብሪካዎች የሳይንስ እና ተክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው። በብዙ መንገደ የሰውን ፍላጎቶች እያሟሉ ነው። በሌላ በኩል ግን ሳይታወቅ በተፈጥሮ ባህሪያቸው አየርን እና ውሃን የሚበክሉ ኬሚካሎችና በአጠቃላይ የሰውን እና የዕጸዋትን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ፣ የተፈጥሮ ህይወት እየተዛባ ነው። ይህ ተዛብቶት የሚስተካከለው በተጠናከሩ እሴቶችና በራሱ በሳይንስ እና ተክኖሎጂ ተጋግዞት ነው።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*