“እርድ data” (ሳማንታ ፓወርን ለቀቅ!! ማጣሪያህን ጠበቅ!!) | ዋጋዬ ለገሰ – ክፍል 2

ይሄ ጽሁፍ ከሳምንቱ የቀጠለ ሳይሆን ከዚህ ሳምንት የተገኘ ነው። በሳማንታ ፓወር ምክንያት ሚዲያና ጋዜጠኝነትን መታዘቤን ያትታል። የሴትዮዋም የድርጅቷም ሆነ የሃገሯ አድናቂ አይደለሁም። የኢትዮጵያና የሱዳን ጉብኝቷን በተመለከተ በሚዲያ በወረደባት የወቀሳ ናዳና በተሰጣት አጉል ስም ግን አልስማማም። “ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማግኘት መጥታ እምቢ ተባለች፤ ተናድዳ ተመለሰች፤ የአማራ ልዩ ሃይል ከምእራብ ትግራይ ይውጣ አለች፤ በሱዳን በኩል ኮሪደር ይከፈት አለች” ምናምን የሚሉ ዜናዎችን እንደ ዶፍ በማዝነብ ተጠምዶ የከረመው ሚዲያ በሆነ አካል የተጠለፈ ይመስላል። የሴትዮዋን መምጣት ሰበብ አድርጎ የራሱን ጉዳይ ከግብ ሊያደርስ የሞከረ ዘመቻ ነበር። አብራራለሁ!

ቬሪፋይዱአካውንት

የሳማንታ ፓወርን ትዊተር አካውንት ትክክለኛነት ያረጋገጥክባቸውን ምክንያቶች እኔም ሳላስባቸው አልቀረሁም። ለምሳሌ፤ የአሜሪካና የሃገርህን ወቅታዊ ውዝግብ ታስታውሳለህ፤ በቅርቡ በአንዳድ የሚዲያ ውይይቶች ላይ ‘ሳማንታ ፓወር የተናገረችው’ እየተባሉ የሚቀርቡትን ሃሳቦች አዳምጠሃል፤ የውጭ ጉዳዩ ኔድ ፕራይስ ሴትዮዋ አዲስ አበባ ከመድረሷ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የሰጠውን ብሪፊንግም ታክልበታለህ፤ የምታምናቸውና ከውስጥ ምንጮቻቸው የሚቀዱ ተንታኞችህም ይኖሩህ ይሆናል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ፤ “ቬሪፋይድ” የሚለውን በመመልከትህ ምንም አልጠረጠርክም። ስለዚህ፤ ትዊቶቹን ሁሉ የሴትዮዋና የድርጅቱ አቋም አድርገህ ብትወስድ ብዙም አያስገርምም። ብዙዎች የገጹን ትክክለኛነት ለማሳመን የሚያቀርቡት ቁልፍ ምክንያትም ቬሪፊኬሽን ላይ የተንተራሰ ነው። “ለመሆኑ ቬሪፋይድ የሚለው ብቻውን ማረጋገጫ ይሆናል ወይ?”

አይሆንም። በቅርቡ ዘ ጋርዲያን ላይ የወጣው ዜና፤ “ትዊተር፤ የአንድን ታዋቂ ደራሲ ፌክ አካውንት ቬሪፋይድ ብሎ ሲያምታታ በመቆየቱ ይቅርታ ጠየቀ” ሲል አስነብቦናል። “Twitter admits it verified fake account of author Cormac McCarthy” ብለህ ፈልገው። ይህቺ ዜና፤ ያለሴትዮዋ ፈቃድ ሌላ አካል ቬሪፋይድ አካውንት በስሟ ሊከፍትባት እንደሚችል አንድ ማሳያ ትሁነን። የቬሪፋይድ አካውንት ባለቤት የመሆኛ መስፈርቶቹን በዝርዝር ስታያቸውም ለማጭበርበር ያን ያህል አስቸጋሪ አለመሆኑን ትረዳለህ። ሶስተኛ የመጠራጠሪያ ምክንያትም አለ። በእሷ ፈቃድ (ግን ባላወቀ ስታይል) ልታስከፍት የምትችልባቸው መንገዶችም ሊኖሩ ይችላሉ። አንዳንዴ የግል አቋምህን ለመግለጽ የምትቸገርባቸው ግን የምትፈልግባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ እንደዚያ ልታደርግ ትችላለህ። ነገርዬው የማያዋጣ ከሆነብህና፤ “ያንተ ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ ከበዛብህ “የእኔ አይደለም አይቼውም አላውቅም ዝጉልኝ” በማለት ትገላገላለህ። አራተኛ፤ የሳማንታን አካውንት በቬሪፋይድቱ ብቻ አምነን እንዳንቀበል የሚያደርገን ምክንያትም አለ። ሌላ (ሁለተኛ) ቬሪፋይድ የሆነ አካውንት አላት። ለመሆኑ፤ ይሄ አካውንት የእሱዋ ነው? ግድ የለህም ይሄንን አካውንት ጠለቅ አድርገን እንመርምረው፤

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*