ከብሔራዊ ምክክሩ ምን እንጠብቅ? | ዶ/ር ሔሮን ገዛኽኝ

ሰሞኑን ብልጽግና-መራሹ መንግሥት በተለያዩ አጋጣሚዎች ብሔራዊ ምክክር ለማደረግ መዘጋጀቱ ቀዳሚ ዜና ሆኗል። የዓለም ዐቀፉን ማኀበረሰብ ጨምሮ፤ አንድ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አጀንዳ በተመለከተ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢም ስለጉዳዩ አስፈላጊነት ከ9 ወር በፊት በዚህችው እንደ ስሟ በፍትሐዊነት አብዝቶ ለሚሳሳላት አገሩ (ባለአገሩ) ይበጃል የሚለውን ሃሳብ እንዲያንጸባርቅ በምትፈቅድለት መጽሔት ላይ “ብሔራዊ ምክክር” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ አቅርቧል። ዛሬም ስለ ብሔራዊ ምክክር ያወሳው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የባዐለ ሲመት ንግግርና ወቅታዊው ሁኔታ፣ መሰል ሃሳብ ዳግም እንዲያነሳ ገፊ ምክንያት ሆነውታል። ጠቅላዩ በንግግራቸው የብሔራዊ መግባባት ድርድር በቅርብ እንጀሚጀምር ገልጸው እንደነበር ይታወቃልና።

በዚህ ዐውድም ‹ከመጪው ብሔራዊ መግባባት (ድርድር) ምን እንጠብቅ?› የሚል ጥያቄ እናነሳለን፤ (በነገራችን ላይ ይህን ጽሑፍ ለማጠናከር ውስን ሃሳቦችን ከቀደመው መጣጥፌ መዋሴን ከወዲሁ እገልጻለሁ።)

እንደ የትኛውም መሰል አገር፣ እድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ ታሪክም ብዙ ውጣ-ውረዶችን አልፎ ዛሬ ላይ አድርሶናል። በዚህ ሁሉ መሃል በርካታ ስኬቶች እንዳሉት ቢታመንም፤ ቀላል የማይባሉ ጉድፎችንም ስለማስተናገዱ የታሪክ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። ከዚህ አንጻር፣ ባለፉ ታሪካዊ ክስተቶች ላይ አሉታዊ አልያም አዎንታዊ ስሜትን ማንጸባረቅ የሚጠበቅ ነው። ተያያዥ ውዝግብም ተፈጥሯዊ ነው። ቁም ነገሩ የሃሳብ ልዩነቶቹ እንዴት ይስተናገዳሉ? የሚለው ነው። በርግጥ በዚህ በኩል ኢትዮጵያችን ጥሩ የሚባል ልምድ የላትም። የአገራችን ታሪካዊ ስኬቶችም ይሁኑ ስንክሳሮች አወዛጋቢ ሆነው ከመቀጠላቸው በላይ፤ ለበርካታ የንፁሃን ዜጎች እርዛት እና ከፍ ላለ የፖለቲካ አለመረጋጋት ዐይነተኛ ምክንያት ስለመሆናቸው፣ ዛሬ በሰሜኑ ክፍል የብዙሃንን ሕይወት እያጨደ እና በርካቶችን ለጆሮ ለሚከብድ ሰብዓዊ ቀውስ እየዳረገ ያለው የእርስ-በርስ ጦርነት ዋንኛ ማሳያ ነው።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*