ከኦባሳንጆ የምንማረው ድብደባ ወይስ ድርድር? | ጌታቸው ሽፈራው

ትሕነግና የድርድር ባህሪው

የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሶጎን ኦባሳንጆ በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆኖ ለማደራደር ጥረት ማድረግ መጀመሩ ከተሰማ ሰነብቷል። ወደ መቀሌ አቅንቶም፣ ደብረፅዮንን ‹በአውሮፕላን አይደበደብም› ብሎ በተጠለለበት የመቀሌ አሉላ አየር ማረፊያ ቢሮው እንዳገኘው ተነግሯል። የትሕነግንና የፌደራል መንግሥቱን ሰዎች ካገኘ በኋላም፣ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሪፖርት አድርጓል። ወደ ዐማራና አፋር ክልል በመጓዝም፣ አመራሮቹን የማግኘት ዕቅድ እንዳለው አመላክቷል።

የትኛውም ጦርነት በውይይትና በድርድር እንዲፈታ መጠየቁ የተለመደ ቢሆንም፤ በዚህ መንገድ ብቻ ግን ችግሩ አይፈታም። “አደራዳሪ” የሚባሉ ሰዎች ስለተመላለሱ ችግር የሚፈታ ቢሆንማ ኖሮ፡- የመን፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ… በርካታ አደራዳሪዎች ተመላልሰው ነበር። በዓለም በተከሰቱ ግጭቶች ከተሳኩ ድርድሮች ይልቅ፤ በየጊዜው የከሸፉት ስፍር-ቁጥር የላቸውም። ኦባሳንጆ የያዘው ደግሞ እንዲሁ ቀላል የሚባል አይደለም። በብዙ ምክንያት።

ትሕነግን የመሰለ ድርድርን የጠላት ማሰናበቻ በማድረግ የጎደፈ ታሪክ ያለው ቡድንን ማመን ለማይታረም ስህተት ያጋልጣል። አያሌ የፖለቲካ ኃይሎችን በድርድር ስም አዘናግቶ የመታበት ልማዱን ‹እንለፈው› ቢባል እንኳ፤ የዛሬ ዐመት ባዘጋጀው ሰነድ፣ ድርድርን ዋነኛ የጠላት መምቻ ስልት አድርጎ እንዲህ ሲል በግላጭ ማስፈሩን አንዘነጋውም፡-

‹‹…ድርድር (Negotiation) አንዱ ጠቃሚ የትግል ገጽታ ሆኖ ይቀጥላል። በበኩላችን ይህንን የትግል አግባብ ተጠቅመንም ቢሆን፣ ጠላትን የምናንበረክክበት ጠቃሚ መሳሪያ አድርገን በስፋት ልንሠራበት የሚገባን ነው። ይህም አስቀድመንም ቢሆን የሰላምና አገር የማዳን ጥሪ በሚል በይፋ ጀምረነዋል።››

እናሳ፣ ድርድርን ዋነኛ ማጥቂያ አድርጎ ካስቀመጠ ቡድን፣ ምን መልካም ነገር ይጠብቃል? ያውም፣ ደብረፅዮን በአንድ በኩል ስለድርድር እያወራ፤ ፃድቃን በሌላ በኩል ‹ጦርነቱን እየጨረስን ስለሆነ ከማንም ጋር አንደራደርም› የሚል መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ?!

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*