ከወደብ እስከ መደብ | ዋጋዬ ለገሰ

ሰሞኑን በዲጂታል ሚዲያው በኩል “አፈትልኮ የወጣ” የተባለውን ሰነድ ከወር በፊት የማየት እድል ገጥሞኝ ነበር። የሰጠኝ ተመስገን ደሳለኝ ነው። ያው “ከየት አመጣኸው?” አይባልም። “የሃይለማርያም ደሳለኝ ወንድም ስለሆነ አንዳንዴ እንዲህ ያሉ ሰነዶች ከማንም በፊት ይደርሱት ይሆናል” ብለህ በጨዋታ ታልፈዋለህ። ለማንኛውም ሰነዱ የቆየ ነው። በሰነዱ የታጨቁት ሃሳቦችም ያረጁ ናቸው። ህወሓት አሳዛኝ ፍጥረት ነው። ምን አይነት ልክፍት እንደሆነ እንጃ። በቃ እሱ የሚያውቃት ሌላ ኢትዮጵያ ያለች ይመስለኛል። ፖለቲካ በዚህ ዘመን እንዲህ የተራ ሰዎች የትወና መድረክ መሆኑ ያሳቅቀኛል። ህወሓት ንቀትና እውቀትን ሲያምታታ የኖረ ብኩን ነው።

በጠብመንጃ ድል እና በኢትዮጵያ ስፋት ውስጥ ቀልጠው የቀሩት ህወሓቶች ከሞቱ ቆይተዋል። መኖራቸውን ለማሳመን በሚሰሩት ድራማም አለመደነቅ አልችልም። የዚህ ቡድን ዋና ችግር የአቅም ነው። ከጨበጠው ሃይል በብዙ እጥፍ ያንሳል። ህወሓት ከኢትዮጵያ ያንሳል። ለኢትዮጵያ ያንሳል። ከአክሱም ይጠብባል። አድዋ ትገዝፍበታለች። ለወደብ ተፈጥሮ ለመደብ ተሰውቷል። በትንንሽ ጉዳዮች መጠመድ፤ ተንኮልና ሴራን እንደፖሊሲ ማራቀቅ፤ ከዘመን እንዳይታረቅ አድርጎታል።

ዛሬም የብሄር ጨዋታን ለማድራት ያልማል። ኦሮሞ ከጎኑ ሆኖ አማራን እንደሚያወድምለት ያብራራል። በጎሳዎች መካከል በሚጭራት እሳት የአራት ኪሎ እንጀራውን ለማብሰል ይታትራል። ጂኦ ፖለቶክሱም ይተነተናል። የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ሁሉ ከአቢይ መንግስት ተቃራኒ ናቸው ይላል። ራሱን በተለመደው ፌክ ሚዛኑ ያገዝፋል። ኢኮኖሚውን አዳክሞ መንግስትን ለመጣል ሲያልም ታገኘዋለህ። ሲአይኤ ምኑን አሴረው ትላለህ። ለትግራይ ህዝብ ያለእሱ አማራጭ እንደሌለ፤ ለመከራው ካለእሱ የደረሰለት እንደሌ ለረሃብ ጥማቱ መድሃኒት እንደሆነለት በመአት ገጾች ይነግረናል። ያካሄደው ምርጫ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱን እንዳሰፋለት፤ አለምን እንዳስደመመለት ያወራል። ከማንም ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ይነግረናል። ቀጣሪ ፍለጋ ይንከራተታል። ጅብም ይሁን አህያ ሊያዝላቸው ይምላል። ሲጠቃለል፤ የትግራይን ህዝብ “ተበደልክ፤ ሌላው ደርግ መጣብህ፤ በረሃብ ሊያረግፉህ ነው” ወዘተ በሚል የስነልቦና ጦርነት አግቶ የቡድን ጥቅሙን ማስጠበቅ እንደሆነ ሰነዱ ይነግረናል። ይሄ ጨዋታ እኔን ወደዛሬም ወደትላንትም ወደነገም አመላለሰኝ። ትላንትም እንዲሁ ነበር፤ ዛሬም ያው ነው። ነገም በዚሁ ይቀጥላል። ነቅቶ መከታተሉ አይከፋምና፤ በሶስቱም ምእራፎች ህወሓትን ለመፈተሽ እንሞክር፤ ከትላንትም ከዛሬም ከነገም።

ረሃብን እንደካፒታል

አንጋፋው የህወሓት አባል፤ ሰለሞን እንቋይ፤ እኤአ በ1985 በዋና አዘጋጅነት የተሳተፈበት አንዲት ሰነድ አለች። “REST” ትላለች። ስለ ማህበረ ረድኤት ትግራይ ትተርካለች። Max Pebernby በተባለ እንግሊዛዊ ጎረምሳ የመስክ ስራ ተለማማጅ ዋና ጸሃፊነት የተመራች የሚዲያና የዶክመንቴሽን ፕሮጀክት ናት። ማህበሩን ለመካብና ለማግዘፍ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ግን፤ ብዙ ሚስጥር መሳይ መረጃዎች ያወጣል።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*