ከፈተና ወደ ፍተላ – በተመስገን ደሳለኝ

የአንዳንድ አገራት ቤተ-መንግሥት በኪነት ሰዎች ከተያዘ በኋላ፣ የሕዝብ አስተዳደር እና የቴያትር ልዩነት እየተምታታ ነው። ዩክሬንን ከሰናኦር ግንብ ያላተመው ቮሎድሚር ዘለንስኬ የተሳካለት ኮሜዲያን ነበር። ድቡን እየነካካ ለማዝናናት መሞከሩ ግን፣ ከማሳቅ ይለቅ መከራ አምጥቶበታል። ዶ/ር ዐቢይ አህመድም፣ “ሦስት ማእዘን” የተሰኘ ፊልም ጽፈዋል። የድርሰቱ ዘውግ ትራጄዲ በመሆኑ፣ የአገዛዝ ዘመናቸውም፡- ሰላም የራቀው፣ ዜጎች የሚፈናቀሉበት፣ የሚጨፈጨፉበት፣ አሰቀቂ አገዳደል እንደ ትርኢት የሚታይበት፣ የክልል ፕሬዚዳንት በጥይት የደበደቡ ወንጀለኞች “በሌሉበት…” ተብሎ የሚፈረድበት፣ ዓለም በመአት ዓይኑ የሚከታተለው ፕሮጀክት ኃላፊ እንደ ሲሲሊ በዐደባባይ የሚገደልበት፣ ቢሊዮኖች የፈሰሰባቸው ኢንቨስትመንቶች በአንድ ምሽት የሚነዱበት… ሆኗል።

‘ዐዲስ አቋቋም ነው’ የሚሉት ፓርቲም ገንዘብ አወጣጡ፣ የአሜሪካኑን “ሪፐብሊካን ፓርቲ” ያስንቃል። የድግስ ጋጋታው አያጣል ነው። ለአክቲቪስቱ የሚረጨው ደግሞ፣ በሴፍቲኔት የሚተዳደር ሕዝብ “የሚመራ” አይመስልም። ከነጋዴዎች ነጠቃ-መሰል መዋጮ መሰብሰቡንም ይዘነጋል። ከቁማር የተረፈውን የፖለቲካ ሥራንም፣ ችግኝ ወደ መንከባከብና ወደ ቢሮ እድሳት አውርዶታል።

በዚህ ዐውድ፣ ሰሞነኛውን ጉባኤ እና የኦዴፓን ጠቅላይነት እንመለከታለን።

ከጉባኤው ጀርባ

ብልፅግና ከጉባኤው በፊት እንደ “አምታታው በከተማ” የቴያትር ቡድን፣ ናዝሪት ከትሞ ሪሄርስ ቢያደርግም፤ ገዝፈው በወጡ ስህተቶቹ አማተሪሽነቱን አስረግጦ አልፏል። ምርጫ ቦርድ፣ ጉባኤው በድጋሚ እንዲካሄድ ይወስናል ወይስ ያፀድቀዋል? የሚለውን ጥያቄ እያሰላሰልን፣ ዋንኛዎቹን ግድፈቶች እንጥቀስ።

የፓርቲው ሕገ-ደንብ “የኦዲት ኮሚሽን አባላት በጉባኤተኛው በቀጥታ ይመረጣሉ፤” ይላል። ይህ መርህ ሁሉም የፖለቲካ ማኀበሮች የሚገዙበት ነው። ብልፅግና እዚህ ጋ የሠራው ጥፋት ለክፍለ-ዘመኑ ቅሌት አጋልጦታል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈልጉ የአመራር አባል ለ“ፍትሕ መጽሔት” የነገሩትን ምስክር እናድርገው፡-

“ባለቀ ሰዓት ዶ/ር ዐቢይ ከፓርቲውና ከምርጫ ቦርድ ሕግ በመቃረን፣ የክልል ኘሬዚዳንቶችን ጠርቶ ‘ለኦዲት ኮሚሽን የሚሆን ታማኝ፣ ገመና የማያጋልጥ አንድ አንድ ሰው ስጡኝ’ አላቸው። እነሱም ‘ፍፁም ታዛዥ ነው’ ያሉትን ለይተው ሲያቀርቡ፤ ‘በሉ ከአዳራሹ ውጪ ተነጋግራችሁ ሊቀ-መንበርና ም/ሊቀ-መንበር መረጣችሁ አሳውቁኝ’ ስላላቸው፣ በተባሉት መሰረት ተመራርጠው መጡ። ከዚያም፣ ስማቸው ለጉባኤተኛው ተነገረ።”

Continue Reading … 

 

 

 

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*