ወታደራዊ ድሉን የፈተነ የመረጃ ተደራሽነት ውድቀት | ጌታቸው ሽፈራው

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትሕነግ ጥቃት ከደረሰበት ማግስት ጀምሮ ያስመዘገበውን ድል፣ ጫካ ውስጥ የተደበቁ አመራሮቹ ጭምር፣ በይፋ የመሰከሩት ሃቅ ነው። በቅርቡ ሜ/ጀኔራል ፃድቃን ገ/ ተንሳይ ከተጠለለበት የትግራይ ተራሮች ሆኖ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መራራውን ሽንፈት እንደወረደ መናገሩ ይታወሳል። ከዚህ በግልባጩ፣ አሸባሪው ኃይል ጨርሶ አለመደምሰሱን ለማሳየት ሲጋጋጡ የከረሙት በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቹ እንደሆኑ በበቂ ታዝበናል። ይህ ድጋፍ የተወሰኑ ምዕራባውያንን እና ሚዲያዎቻቸውንም እንደሚያካትት ልብ ይሏል።

ይህንን ተንተርሶ፣ በደረሰበት ሽንፈት በየሸጡ ተደብቆ የነበረው የትሕነግ አመራር፣ ከወራት በኋላ በፎቶ እና በቪዲዮ እየተከሰተ ‹አልሞትኩም› ማለትን እንደ ጀብዱ ይዞታል። ሠራዊት እያሰለጠኑ፣ ዐዲስ የተቀላቀሏቸውን ታዋቂ እና ምቾት ላይ የነበሩ ግለሰቦችንም እያስተዋወቁ ፕሮፓጋንዳውን አጡፈውታል። ‹ዱቄት› ሆነ የተባለው ኃይል በፕሮፓጋንዳ ብዛት ነፍስ የዘራ መምሰሉ፣ እንደ ስጋት ሊታይ የሚገባ መሆኑን መረዳት የወታደራዊ ሳይንስ ‹ሀሁ…› ነው። ለዚህ ደግሞ ዋንኛው ተወቃሽ የመንግሥት የመረጃ ቁጥጥር፣ ስርጭትና ተደራሽነት ደካማ መሆን በምልዓት የሚያስማማ እውነት ነው። መቼም አያሌ ሚዲያዎችን፣ የሚዲያ ስትራቴጅስቶችን፣ አማካሪዎችን፣ ተከፋይ ፕሮፓጋንዲስቶችን… ያሰለፈ መንግሥት፣ ጫካ በተደበቀ አሸባሪ ቡድን ደጋፊዎች ፕሮፓጋንዳ መበለጥን የመሰለ ክስረት የለም።

የመረጃ ተደራሽነት ውድቀት እንዴት?

የማርክሲዝም ሌኒንዝም መዝገበ-ቃላት ፕሮፖጋንዳን፡ – ‹‹ጠለቅ ያለ ርዕዮተ-ዓለማዊ ይዘትና የስርጭት ስልት ያለው፣ በአንድ የተወሰነ ጉዳይ ላይ ለጥቂት ወይም በርከት ላሉ ሰዎች ብዙ ሐሳቦች የሚተላለፉበት ስልት ነው፤›› በሚል ያፍታታዋል። ከርዕዮተ-ዓለም አኳያ ‹ውሸትን እውነት አስመስሎ የሚቀርብበት የሐሳብ ማስተላለፊያ ስልት› እንደማለት ነው። ….

Continue Reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*