ወያኔ ሲደመሰስ – ኢኮኖሚውስ? | ናኦል ጌታቸው

የኢንዱስትሪ አብዮት መነሳትን በመሰሉ ኹነቶች፣ በአውሮፓ ያለው ‹‹የምርት ዘይቤ›› መለወጥ ጀምሯል። በዚህም ከእስከዛሬው በተለየ መንገድ፣ ኢንዱስትሪው በባሪያ ጉልበት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ተፈልጓል። ይህንን ተከትሎም፣ በዚሁ ሰሞን በ‹‹ብረትና ደም›› ተደግፋ “የጀርመን ኢምፓየር”ን የመሰረተችው አገር የመጀመሪያው ቻንስለር ኦቶ ቫን ቢስማርክ፣ የአውሮፓ አገራት ዓይናቸውን የጣሉባትን አፍሪካ ተስማምቶ ለመቀራመት የሚያስችለውን ስብሰባ ጠራ። እ.ኤአ ህዳር 15/1884 ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ “የበርሊን ኮንፍራንስ” የሚል ስያሜ በያዘው መድረክ የታደሙት 12 የአውሮፓ አገራት እና ላይቤሪያ ላይ ፍላጎት የነበራት አሜሪካ አፍሪካን ለመቃረጥ ቢላቸውን ስለው ተቀመጡ። የቤልጂየሙ ሊዮፓርድ ሁለተኛ እና ቢስማርክ ቶሎ እንዲያልቅ የጠሩት ስብሰባ 104 ቀናትን ፈጅቶ፣ የካቲት 26 1885 (እ.ኤ.አ) ተጠናቀቀ። ያኔ የተላለፉ ውሳኔዎች ግን፣ በዛሬዋ አፍሪካ ድረስ የተራዘመ እልፍ ድንበር ነክ ደዌዎችን አዋልዷል።

ይህም ሆኖ፣ የጀርመኑ የቅኝ መግዛት ስብሰባ ድንገተኛ ክስተቶችም ነበሩት። አሜሪካ ቅኝ ከመግዛቱ ስምምነት ራሷን ስታወጣ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወራሪውን ክንድ በመስበር ቅኝ ያልተገዛች አፍሪካዊት ለመሆን ችላለች፤ (ላይቤሪያም፣ የአሜሪካንን ውሳኔ ተከትሎ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ቅኝ ያልተገዛች አገር ሆናለች።)

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ‹‹ቅኝ አልገዛም›› ያለችው አሜሪካ፤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የቀዝቃዛውን ጦርነት ማሸነፏን ተንተርሳ፣ የእጅ አዙር ቅኝ ገዢ መሆኗ ግን አልቀረም። በስብሰባ “ቅኝ እንግዛ” ብለው ከወሰኑ ከዘመናት በኋላ፣ መልሰው በስብሰባ ‹‹ቅኝ አንግዛ›› ያሉት የአውሮፓ አገራትም አፍሪካን አልተዉዋትም።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*