
ስለዐድዋ ድልም ሆነ ስለስመ-ጥር አርበኞች ተጋድሎ፣ ዐመት ጠብቆ ሲዘከር ኖሯል ይባል እንጂ፤ ይህ ዐይነቱ አይረሴ የድል ብስራት በየቀኑ ቢደረግስ?! ሕዝብን የሚያጀግን እንጂ፣ የሞኝ ተግባር አይደለም። የዐድዋ ድል እንኳንስ ኢትዮጵያውያን፣ ከመላው አፍረካውያንም አልፎ፣ በዓለም ዙርያ ላሉ ጥቁር ሕዝብ ጭምር በመሆኑ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል በመንሳቱ ረገድ፣ ሁለት ጊዜ ያህል በዘመን ልዩነት ያሳካችው ታለቅ የተጋድሎ አጀብ ጉድ የሚያሰኝ ነው።
ከዐድዋው ጦርነት ላይም ሆነ ሁለተኛው የጣልያን ወረራ ድል በኋላ፣ እንደ አገር በታላቅ ድባቴ፣ ድንዛዜ ወይም ፍዘት የኖርን ሕዝቦች እንመስላለን። በረባ-በልረባ እርስ- በርስ ስንላፋና ስንጓተት፣ በተቋም ምስረታ መስፋፋት ላይ ዳተኛ ሆነናል። በሥነ-ልቦና ረገድም ያብሮነት የጋራ እሴትና የጋራ ግብ ላይ ያለው መሸርሸር ግልፅ ማሳያ ነው።
ዛሬ ላይ ዓለም እኛን የሚያውቀን በተደመመባቸው ታላላቅ የጦርነት ድሎቻችን ሳይሆን፤ የቅርብ ጊዜ ኩነታችን በሆኑት ችጋር፣ እርዛት፣ ስደት… ወዘተ ነው። ስለጀግንነቱና ኩራቱ እየሸለለ፣ ነገር ግን አገርን ከዘርፈ-ብዙ ችግሮች የሚታደግ ሥራ ሳይሰራ የሚኖር ማኀበረሰብ፣ ከአዘቅቱ መውጣት እንዴት ይቻለዋል? የዚህ ድል ብስራት ሰርክ መዘከሩ ብቻ በቂ አይሆንም። ጥንት አባቶቻችንና እናቶቻችችን ሠርተውና ጀምረውት የሄዱትን ማስቀጠል ይኖርብናል።
የዐድዋ ድል የትናንት ኩራታችን ላይ ተንተርሰን ዛሬያችንን ወቅሰንና ተቆጭተን፣ ነገ ከድባቴያችን ለመንቃት እንደማትጊያ ስንቅ ልንጠቀምበት ይገባል። የቱንም ያህል ጊዜ ፈጅቶ፣ የቱንም ያህል ዋጋ ተከፍሎበት ታሪካችንን ለማደስ፣ ……
Be the first to comment