
ሕወሓት በስሌት የጀመረውን ጦርነት፣ ብልጽግና በስሜት ቢያሸንፍም-ቅሉ፣ በብላሽ አስቀርቶት ዋጋ እየከፈለ ነው። በደም የተገኘው ድልም፣ በፖለቲካ ውሳኔ መቀልበሱ፣ የጦርነቱን ሜዳ ቀይሮታል። ርግጥ እዚህ ጋ አንዳንድ ክህደቶችና ሴራዎች ላይጠፉ ይችላሉ። መቼም ለወራት በዋሻ ተሸሽጎ የከረመ ቡድን፣ ድንገት በወታደራዊ መኪናዎች ታጭቆ፣ በታንኮች ታጅቦ፣ መድፍ እየተኮሰ በተባረረበት ከተማ ለመንጎማለል፣ የመለኮትን ፍጡነ-ረዴት ይጠይቃል።
የሆነው ሆኖ፣ ሕወሓት ዐማራ እና አፋር ክልልን ከመውረሩ በፊት፣ ወታደራዊ እና ፖቲካዊ የአመራር አባላቱ (በውጪ ያሉትንም ይጨምራል)፣ ለ6 ቀናት በZoom ምስጢራዊ ስብሰባ ማድረጋቸውን በመከላከያ ተጠልፎ፣ በማኀበራዊ ሚዲያ በተለቀቀው ሰነድ ተጋልጧል። ይህ መረጃ አንድም ብዙ ትኩረት ባለማግኘቱ፤ ሁለትም ከድርጅቱ ወቅታዊ መክለፍለፍ እና ከአሜሪካ “ተደራደሩ” ጀርባ የተሸረበውን ሴራ ያፍታታዋል በሚል፣ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ተደርጓል።
“የውይይቱ ዋንኛ ዓላማዎች ሁለት ናቸው:-
ሀ) ትግራይ ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን ለማድረግ፣ ሊሠራ የሚገባው ውስጣዊና ውጫዊ የፖለቲካ ሥራዎችን መረዳትና መከፋፈል።
ለ) ትግራይ ጦርነቱን አሸንፋ እንድትወጣ ማስቻል አማራጭ የሌለው ነው።
በውይይታቸውም በሚከተሉት ነጥቦች የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
- ትግራይን በሀገረ-መንግሥትነትን ለመመስረት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት አብዮቶች መፈጠር አለባቸው።
- የኦሮሞ ብሔር ምንም የጋራ አገራዊ ማንነት ስለሌላቸው፣ በአገራዊ ስሜት ሊነሱ ስለማይችሉም ጭምር፤ የአዲስ አበባን ጉዳይ ምክንያት በማድረግ፣ ‘ፊንፊኔ ኬኛ’ ብለው እንዲያምፁ ከኦነግ ጋር ወሳኝ ትብብር መፍጠር። ለዚህም ተጋሩዎች አስፈላጊውን ዋጋ ከፍለው የፊንፊኔን ጉዳይ በማነሳሳት ‘የኦሮሚያ አካል ካልሆነች’ በሚል ጥያቄ አዲስ አበባ ላይ እሳት መጫር።
- በአፋር እና በሶማሌ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ማባባስ፤ አፋር ላይም በትግራይ በኩል ጦርነት በመክፈት existential threat እንዲሰማው ማድረግ። በሶማሌ እና በትግራይ መገደል የሚጀምረው አፋር ሳይወድ በግዱ ኤርትራ እና ጅቡቲ ካሉት አፋሮች ጋር ይተባበራል። ይሄን ስልት ለማፍጠን ከአፋር ጋር የመሬት ጥያቄ በማንሳት ወደ ውጊያ መግባት። በውጊያው የሚያጋጥመው ኪሳራም የሥነ-ልቦና ውድቀት ስለሚያደርስበት በኢትዮጵያ ተስፋ ይቆርጣል።
Be the first to comment