የሕወሓት ተለዋዋጭ ቁመና እና አንድምታው | ዶ/ር ሔሮን ገዛኽኝ

ኢትዮጵያ ምናልባትም በታሪኳ ከገጠሟት ጥቂትና እጅግ ፈታኝ አጋጣሚዎች አንዱ ዛሬ ያለችበት የጭንቅ ጊዜ ይመስለኛል። ዘጠኝ ወራትን ያስቆጠረው የሰሜኑ ጦርነትም ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላው እየተሸጋገረ ስለመሆኑ፣ በሁለቱም ተዋጊ ወገኖች የሚጎሰሙት የክተት ሠራዊት አዋጆች ዋንኛ ማሳያዎች ናቸው። በርግጥ ክፉውን ያርቅልን እንጂ፤ በበኩሌ እጅጉን የሚያስፈራኝ ከሆነው ይልቅ፣ መጪው ነው።

በዚህ ዐውድ ተጠናክሮ የቀጠለው የእርስ-በርሱ ጦርነት፣ ሕወሓትን የት ያደርሰው ይሆን? ከሁለንተናዊ ቁመናው አኳያ በትግራይ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው አንድምታስ ምን ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ እፈትሻለሁ። የጽሑፌ ማጠንጠኛ የሕወሓት ተለዋዋጭ ቁመና የሚኖረውን ክልላዊ፣ አገራዊ እና ቀጠናዊ ተገማች አንድምታ ላይ ነው። ርዕሰ-ጉዳዩን በደንብ ለማፍታትም የ“ቢሆን ሃሳብ”ን፣ ከመረጃዎች ጋር በማሰናሰን ለመጠቀም እሞክራለሁ።

የቢሆን ሃሳብ 1:- ሕወሓት ጨርሶውኑ ቢጠፋ

መንግሥት እንደሚለው ሕወሓት ጨርሶውኑ ቢጠፋ፣ የትግራይን ባላውቅም ቀሪው የአገሪቱ ክፍል እፎይ እንደሚል እገምታለሁ። ይሁንና ሕዋታዊነት በትግራይ ከፖለቲካዊ አስተሳስብነትም አልፎ፣ ከነፍስ እስከ መዋሃድ መሸጋገሩን ስናስታውሰው ደግሞ፣ ሕወሓትን የማጥፋቱ ዘመቻ ይሳካል ብሎ ለማመን ይቸግራል። እኔም ራሴን ከዚህ ጎራ እመድባለሁ።

የቢሆን ሃሳብ 2:- ሕወሓት እጅጉን ቢዳከም

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*