የሕወሓት ከማዕከላዊ መንግሥት መራቅ እና የ“ትግራይ ተከባለች” ተረክ! | ግርማ ሰይፉ ማሩ 

ለፈው ጽሑፌ የትግራይ ሕዝብ ከሞላ ጎደል ከሕወሓት ጋር የተሰለፈበትን የ“ቢሆን አማራጮች” በአጭሩ ለማመላከት ከሞክርኩ በኋላ፤ የበለጠ ያሳመነኝ የ“ጋራ ጠላት ፈጠራ”ው እና የ“ተከበናል ትርክት” ሊሆን እንደሚችል ሃሳቤን አስፍሬ ነበር። በዚህ ዐውድ ደግሞ ሕወሓት ከማዕከላዊ መንግሥት ቀስ በቀስ ለምን ሸሸ? ተገፍቶ ወይስ በሌላ ምክንያት? በሚሉት እና በ“ተከበናል” ትርክት ላይ አተኩራለሁ።

ከዚህ ቀደም ከቀጣዩ ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ድምዳዬን በመጽሔፌም ሆነ በአንድ ጽሑፌ ማስነበቤን አስታውሳለሁ። የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በአንድ ሬስፕሽን ላይ ተገናኝተን፡- “አቶ መለስ ዜናዊ ሥልጣን ይለቃል ብለህ ታምናለህ ወይ?” ብለው ላቀረቡልኝ ጥያቄ፣ “አዎን!” የሚል መልስ ከሰጠኋቸው በኋላ፤ የሚለቀው ግን ለአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንጂ፤ ለዐማራ እና ኦሮሞ እንደማይሆንም ጭምር ጠቅሼ ነበር። እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስኩበት ምክንያት ለዐማራ እንዳይሰጥ፣ በ“ዐማራ ገዢ መደብ” የተፈጠረው ትርክት ሌሎቹ የብሔር ድርጅቶች እንዳይስማሙ እንቅፋት ከመሆኑ በተጨማሪ፤ በወቅቱ የብአዴን መሪዎችም ዝግጁ ስላነበሩ ነው። ለኦሮሞ ከሰጠ ደግሞ፣ መልሶ ሊያገኘው አይችልም ብዬ ስላመንኩ ነበር። ለአቶ ኃይለማሪያም ከሰጣቸው ግን፣ በማንኛውም ጊዜ በሲዳማ ልሂቃን ግፊት ለማንሳት እንደማያዳግተው (ኃይለማሪያም ከደቡብ ክልል እንዴት እንደተነሱም ይታወቃል) በግልጽ የሚታይ ሃቅ ነው።

በዚህ ምክንያት ሕወሓት ከጀርባ ሆኖ “በፑቲን ስታይል” ሊመራ የሚችልብት ስልት ተቀምሮ ነበር። ይሁንና እቅዱ ከመተግበሩ በፊት ጠቅላይ ሚንስትር መለስን ሞት ስለቀደመው፤ እሱ ባሰበው ልክ ባይሆንም፣ ሕወሓት ብቸኛ አማራጩን አቶ ኃይለማሪያምን ጠቅላይ ሚንስትር አድርጓል። ይህ ደግሞ ብርቱ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳይኖር አግዷል። ለዚህም ነው፣ የሕወሓት ሹመኞች እና ጄኔራሎች አብረዋቸው ያሉትን አገልጋዮች በመናቅ ቅጥ-ያጣ ዘረፋና ውንብድና ውስጥ ሲገቡ ከልካይ ያልነበረው።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*