የሚሸሽ ሠራዊትን በተመለከተ | ጎበዜ ሲሳይ

በዐማራ ክልል፣ በሰሜን ወሎ ዞን ስር ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ ስድስቱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ናቸው። መንግሥት ቀድሞ ሲል የለቀቀው የራያ ቆቦ ወረዳን ሲሆን፤ የወረዳው መቀመጫ የሆነችውን ቆቦ ከተማን ከመልቀቁ በፊት የተከሰተው ነገር ከተማዋ በጥላት እጅ እንድትወድቅ ገፊ-ምክንያት ነው።

ይኸውም፣ ከጮቢ በር (ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኝ አነስተኛ ቀበሌ) የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት፡ – ‹አዛዦቻችን የሉም፤ የሚያዋጋን ጠፋ፤› በሚል ስበብ ወደ ከተማዋ ይፈሱ ነበር። በዚህም አንድ ጥይት ሳይተኮስ የከተማው ሕዝብ ድንጋጤ ውስጥ እንዲገባ እና በጠላት ኃይል እንዲያዝ ተደርጓል። በተለይ ሠራዊቱ በከተማው ውስጥ ተበታትኖና የሚሰበስበው አጥቶ መታየቱ በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ነው። መቼም በእንዲህ ዐይነቱ የጦርነት ጊዜ፣ ያውም በከተማ ውስጥ ከሠራዊቱ አባላት ውስጥ አንዳንዶቹ የደንብ ልብሳቸውን ቢለብሱም ባዶ እጃቸውን፣ አንዳንዶቹ ከእነ ትጥቃቸው፣ አልፎ አልፎ ደግሞ በሲቪል ልብስ ትጥቃቸውን አንግተው ከመታየታቸው አኳያ፤ የቆቦ ነዋሪ ‹ይሄ ነገር ሌላ መልክ ይዟል› ወደሚል ጥርጣሬ ቢገባና አካባቢውን ቢለቅ የሚስፈርድበት አይደለም።

በወቅቱ ወታደሮቹ ለምን ተመለሱ? የሚለው ጥያቄ የሁሉም ነዋሪዎች በመሆኑ፣ መንገድ ላይ ያገኙትን ወታደር እያስቆሙ ሲጠይቁ የሚሰጧቸው ምላሽ የተለያየ ነበር። አንዱ ‹ተመለሱ ተብለን ነው› ሲል፤ ሌላው የሚያዋጋን ጠፋ› ይላል። ግማሹ ደግሞ ‹ምግብ (ሬሽን አልቀረበልንም› በማለት ይመልሳል። በዚህ ላይ የውጊያውን ዐይነት፣ የጠላትን አሰላለፍ፣ የወገን ጦርን ጥንካሬ እና ድክመት ሳይቀር፣ ከወታደራዊ ዲስፕሊን ባፈነገጠ መልኩ ጠጋ ብሎ ለጠየቃቸው ሁሉ ያካፍላሉ። አብዛኛዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው በየደረሱበት ከወጣቱ ጋር ለመላመድ ጊዜ እንዳልፈጅባቸውም ተስተውሏል። በበኩሌ ከሁኔታው የታዘብኩት አንድ የታጣቂው ቡድን መረጃ አቀባይ በቀላሉ የሚፈልገውን መረጃ ከእነዚህ ወታደሮች ማገኘት እንደሚችል ነው።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*