የሰሜኑ ጦርነት ፪ | ዳሰሳ

ቀዳሚዎቹ ገጾች፣ ሕወሓት፣ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የጀመረውን ንትርክ፣ በጦርነትና በሽብር ለመበየን መወሰኑን ከራሱ ሰነድ በስፋት አይተናል። በዚህኛው ክፍል ደግሞ፣ ከጦርነቱ ዋዜማ እስከ ዛሬ ያለውን እንመለከታለን።

…ድርጅቱ፣ የአራት ኪሎ ሽንፈቱን ለመቀልበስ ሥራ የጀመረው መቀሌ በደረሰ ማግስት እንደሆነ መረጃዎች አሉ። አንዱን እንጥቀሰው።

ሰኔ 16/2010 ዓ.ም።

በእዚህ ዕለት በመስቀል ዐደባባይ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ላይ ቦንብ ተወርውሮ እንደነበረ ይታወቃል። የሴራውን አቀነባባሪ በርግጠኝነት ‘እገሌ’ ብሎ መናገር ቢቸግርም፤ ሕወሓት ስለእቅዱ ያውቅ እንደነበረ ግን ማሳያዎች አሉ። ለዝርዝሩ የፍትሕ ወታደራዊ ምንጭ፡-

“ሰኔ 15 ምሽት ከፍቼ ከተማ ሁለት ሻምበል ተወጊ መሀንዲስ ሠራዊት አዲስ አበባ ገብተው ጃንሜዳ አካባቢ እንዲሰፍሩ ተደርገ። እነዚህ ወደ 700 የሚጠጉ ወታደሮች ከፍቼ ሲነሱ፣ ለሦስት ቀን የሚሆን ደረቅ ሬሽን (ብስኩት) ታድሏቸዋል። ይሄ፣ በወታደራዊ ቋንቋ ‘የምትሄደው ለግዳጅ ነው’ እንደማለት ነው። በርግጥ በወቅቱ ከትግርኛ ተናጋሪ ወታደሮች በቀር፤ ስለመጡበት ግዳጅ ለማናቸውም አልተነገራቸው። አዛዣቸውም ኮሎኔል ሰመረ የተባለ የሕወሓት ሰው ነው። እቅዱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከመስቀል ዐደባባይ በሰላም ከተመለሱ፣ ምሽቱን ከቤተ-መንግሥቱ ጠባቂዎች ጋር ተባብረው መፈንቅለ-መንግሥት ማድረግ ነበር።”

ታዲያ እንዴት ከሸፈ?

“የግድያው ሙከራ በተደረገበት ዕለት ወደ 11 ሰዓት ገደማ፣ በድንገት ቤተ-መንግሥቱን ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በሙሉ ግቢውን ለቀው እንዲወጡና ለገዳዲ እንዲሰፍሩ ተደረገ። በእነሱ ቦታ ደግሞ፣ ሁለት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሻለቃና አንድ የዐማራ ልዩ ኃይል ሻለቃ ተተክተው ተመደቡ። ይህ ድንገቴ ቅየራም እቅዱን አከሸፈው። ጃንሜዳ የሰፈሩት የሁለቱ ሻምበሎች አዛዥ ኮሎኔል ሰመረም የዚያኑ ቀን ወደ መቀሌ ኮበለለ። በኋላ በተደረገ ግምገማ የመሀንዲስ መምሪያ ዋና አዛዥ የነበረው ሜ/ጄ ሙሉ ግርማይ ‘ስለጉዳዩ የማውቅ ነገር የለም’ ብሎ ክዷል።”

ሌሎች ሙከራዎች በሁለቱም ወገን እንደነበሩ አስታውሰን እንቀጥል።

Continue Reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*