የትሕነግ የጦር ወረራ አፈጻጸም | ቴዎድሮስ ታደሠ

በፓርላማው በአሸባሪነት የተፈረጀው ትሕነግ የትግራይን ሕዝብ በማስነሳት፣ በዐማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ወረራ መፈጸሙ ይታወቃል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወረራው የደረሰውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና ቁሳዊ ውድመት ለማወቅና እና የአፈፃፀሙን ሁኔታ ለመረዳት፤ ወረራው ያስከተለውንና በቀጣይ የሚያስከትለውን የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበረሰባዊና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ለመለየት፣ ሁለተናዊ ቀውሱን ለአገር ውስጥም ሆነ ለዓለም ዐቀፉ ማኀበረሰቡ ለማሳወቅና ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ የአስቸኳይና የአጭር ጊዜ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም አንድ ቡድን አቋቁሞ የዳሰሳ ጥናት አድርጓል። በዚህ ጽሑፍም የጥናቱን ግኝት የሚመለከት ዳሰሳ ይቀርባል። የጥናቱ ማዕከል በዐማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ላይ የደረሰውን ውድመት የሚመለከት ይሆናል።

  1. የጦር ወረራው አፈፃፅም

የጥናት ቡድኑ የዓይን እማኝ ከሆኑ ግለሰቦች፣ ወራሪው ኃይል ስለሚያሰልፈው የተዋጊ ዐይነትና ብዛት ከተቀበለው መረጃ አንጻር፣ ወራሪው ጦርነቱን ሕዝባዊ እንዳደረገው በግልጽ መረዳት ይቻላል። የትግራይ ወራሪ ኃይል ህጻናትን፣ ሽማግሌዎችንና ነፍሰ-ጡር እናቶችን ሳይቀር በተዋጊነት እንዳሰለፈና አነስተኛ መንደርን ለመቆጣጠር እንኳ በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን እንደሚያሰማራ ለማወቅ ተችሏል።

ይህም “ጦርነቱ የመላው የትግራይ ሕዝብ ነው” በማለት በሚዲያ የተናገሩት መሬት ያለ እውነታ መሆኑን፤ በሌላም በኩል በየመገናኛ-ብዙሃኑ የትግራይን ሕዝብ በጅምላ ወደ ጦርነት ለመማገድ ሲያደርጉት የነበረው ቅስቀሳ የጥፋት ፍሬ ማፍራቱን ያረጋግጥልናል። ከነሃሴ 5 እስከ 14 2013 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን ለዘጠኝ ቀናት የቆየው የትግራይ ኃይል ከተማዎችን፣ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን በወረራ በሚይዝበት ጊዜ የማሸበር፣ የማግባባት (የማታለል)፣ የመዝረፍና የማውደም ስልቶችን በቅደም-ተከተል እንደተጠቀመ በጥናቱ ለማወቅ ተችሏል። ይኸውም ዐዳዲስ ቀጠናዎችን ከመውረሩ በፊት፣ በዙሪያቸው በቀላልና ከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት በነዋሪዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር፣ ሰብዓዊ ጥፋት በመፈፅም፣ ቁሳዊ ውድመት በማድረስና ከፍተኛ ሽብር በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በመንዛት እንደሚቆጣጠራቸው ታውቋል።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*