“የአሜሪካ ሲቪ” | በዋጋዬ ለገሰ

ሰሞነኛው የጂ7 ስብሰባ መልስ የባይደኗን አሜሪካ የበለጠ የመተዋወቅ እድል አግኝተናል። “እኔና በዲሞክራሲ የበለጸግነው ስድስቱ አጋሮቼ፤ ቻይናን የምንገዳደርበት፤ የምንመክትበት አዲስ እቅድ ይዘን መጥተናል” አሉ። የእኛን ስታንዳርድና፤ መለያ በሚገልጹ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ደሃ ሃገራትን እናጥለቀልቃለን፤ የቻይናን ጥራት የለሽና በብልሹ አሰራር የተተበተቡ የግንባታ ፕሮጀከቶፐች የምንመታበት መሳሪያችን ነው፤ እስከ 45ትሪሊዮን መድበንለታል” አሉን። ሌላም ብዙ ብለዋል። “የባይደን እቅድ” ተብሎም ሊሞካሽ ዳድቶታል። ያው ዋናዋ ጉዳያቸው ቻይና ናት። እነሱም በአደባባይ ተናግረውታል። ትላንትም ይናገሩት ነበር፤ ወደፊትም ይደጋግሙታል።

ከሁለት አመት በፊትም፤ የትራምፕ መንግስት በአፍሪካ ዙሪያ ያቀረበው አዲሱ ስትራቴጂ “የበለጸገች አፍሪካ” የሚላት ነገር ነበረችው። ዋና ጉዳያችን የአፍሪካ ብልጽግና ነው ይላል ሰነዱ። ለአፍሪካ አዲስ አካሄድን ይዞ እንደመጣም ያትት ነበር። ሌላም ቀደዳ አለው ውስጡ። ርእሱን የአፍሪካና የዩኤስ ይበሉት እንጂ በዋናነት የሚያወራቅ ስለቻይና ነበር። የወቅቱ የደህንነት አማካሪ ሰነዱን ሲያብራሩ፤ የቻይናን ስም 25 ጊዜ ጠርተዋል፤ ቻይናና ሩሲያ ከሃምሳ አራቱ የአፍሪካ ሀገራት በላይ ስማቸው ዶክመንቱ ላይ ይጠቀሳል፤ ይህቺ ምሳሌ፤ ሰዎቹ ለአፍሪካ ምንም ተጨባጭ ስትራቴጂ እንደሌላቸው ቀላል ማሳያ ናት። ። የሚጨነቁትም ለአፍሪካ ብልጽግናና ደህንነት ሳይሆን በዋናነት የቻይናን በመጠኑ ደግሞ የሩሲያን እድገት ለማመቅ ነው። ጉዳዩዋ ቻይናን ካውንተር ማድረግ ብቻ ነው ። ወይም በራሳቸው አስበው የአፍሪካንም የኤዚያንም ችግር ስለመፍታት አይጨነቁም።

ሰሞኑንም የታየው ይሄው ነው፤ የቻይናን ፕሮጀክት ለመመከቻ እንዲሆነን ለደሃ ሀገራት አዲስ የልማት እቅድ ይዘንላቸው መጣን ሲሉ በአደባባይ ተናገሩ። እንዲህ ያለ በንቀትና በግድየለሽነት የተሞላ ድርጊት ለ21ኛው ዘመን እንዲመጥን ያደረገችው አሜሪካ ናት። አሜሪካ ላለፉት ሃያ አመታት ባንሰራፋችው ሰፊ የሚዲያ ግዛት ያሻችውን በአፉዋ ዘርታ የምታጭድ የወሬ ልክፍተኛ ሆናለች። ይሉኝታ አይነካካትም፤ ውሸቱም ገደብ የለው፤ ተአብዮውም አቻ አልቦ ነው። በዚህ መካከል አብዛኛው ይታዘባል። ይሄንን ለማረጋገጥም በየዲጂታል ሚዲያው ለሰሞነኛው አይነት አሜሪካ መራሽ ዜናዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች መመልከት ይበቀዋል። ለአካዳሚክ ክበቡም በአሜሪካ መሳለቅ ቀላል ስራ ነው። እመነኝ አንባቢ ሆይ! አሜሪካ የቻይናን በአፍሪካ የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚገዳደር ነገር ሊኖራት አይችልም። ከአውሮፓም ብታብር ከላረቲን አሜሪካ የድራገኖቹን ዱካ የሚከተል አቅውም አይኖራትም። አይደለም በተግባር ማሳየት ሃሳቡን ሲያቀርቡት እንኩዋን አልቻሉበትም። የቻይና አፍሪካ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ስላለህ ብቻ የምትሰራቸው አይደሉም። እሱም ቢሆን ያን ያህል አያስታምንም። ነገርዬው ዘርፈ ብዙ ግብአቶችን የሚፈልግ ነው። ጉስቁልና፤ ቁጭት፤ ታታሪነት፤ ጽናት፤ አንድነት፤ ርእዮተአለማዊ መስመር፤የሰው ሃይል፤ አለመጠየፍን፤ ሀገር መውደድ፤ ወዘተ ይጠይቃል፤ አሜሪካ ዘንድ ብዙዎቹ የሉም። ዋሺንግተኖቹ እንደሚነግሩን ሙሉ አይደሉም።ራሳቸውን የሳሉንን ያህል ግግዙፍ አይደሉም። ሆሊውድ ሌላ እነሱ ሌላ ናቸው። ከመረጃ ሃብታቸው፤ እስከ መከላከያ አቅማቸው፤ ከስትራቴጂካዊ እስከ ታክቲካዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ድረስ በትናንሽ ታሪክ የደበዘዙ ናቸው።

ሲአይኤ ዋቴው!” … 

Continue Reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*