የአሜሪካ ሴራ | ሀብታሙ አስማማው

ዓለምን በብዙ መልኩ ከሚፈታተኑ ኃያላን አገራት መካከል አሜሪካ አንዷ ናት። አገሪቱ ኃያልነቷን ተንተርሳም ሆነ በሳጥናኤል ተመርታ በየአገራቱ ላይ ጣልቃ እየገባች የምትሠራውን ፖለቲካዊ ሴራ ለመረዳት እስከ ዛሬ ያፈረሰቻቸውን አገራት መለስ ብሎ መመልከት ይቻላል። “ሳይጠሩት አቤት ባይ የሰይጣን ጎረቤት ነው” እንዲሉ፤ አሜሪካ ሳትጠራ ጣልቃ በመግባት አገራትን ከማፍረስ ጎን-ለጎን ሰው ሰራሽ ጦርነት እና በሽታን ስትፈጥር ከሰይጣን ባልተናነሰ ተግባር ነው።

የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት የነበረው ሂው ጎቻቬዝ በ2006 የ‹‹United Nation›› ስብሰባ ላይ ስለ አሜሪካ ሰይጣናዊ ተግባርም ሆነ በሳጥናኤል ስለመመራቷ እንዲህ ብሎ ነበር፡- “The devil is here, the devil himself right in the House. Yesterday the devil came here and it smells of sulfur still today. This table that I am standing in front of, the president of United State of American came here and talking as the owner of the world.”

“ሳጥናኤል እዚህ አዳራሽ ውስጥ ነበረ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንትም እዚህ ነበረ፤ ዓለምን ሙሉ የተቆጣጠረና እንደፈለገ ማድረግ እንደሚችል ሲደሰኩር ነበር፤” በማለት አሜሪካ ሰይጣናዊ መንፈስ የሚንፀባረቅባት አገር መሆኗን ተናግሯል። አብዛኛው ሕዝብ አሜሪካ የብር ኖቷ ላይ ‘’In GOD We Trust’’ ብላ የፃፈችውን በማየት ብቻ በፈጣሪ የምታምን ይመስለዋል። ነገር ግን፣ አንድ አገር በፈጣሪ የሚያምን ከሆነ እንዴት ፈጣሪ የከለከለውን ግብረ-ሰዶምን ይፈቅዳል? ብሎ ለጠየቀ እውነታውን አያጣውም። አሜሪካ ‹‹In GOD We Trust›› ብላ የፃፈችው ለፈጣሪ ሳይሆን፣ ‹‹In GOD We Trust G-Gold›› ወርቅ እና ማዕድናት ለማለት ነው።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*