የወልቃይት ፖለቲካ (ደባርቅ እና ዘባርቅ) | ወቅታዊ ጉዳይ

ሮጌዋ ኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥቷን ያነፀችውም ሆነ ያጸናችው በተራዘመ ታሪክና በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን መካድ፣ ከብሔር ሥራ- ፈጠራ (ethnic entrepreneur) ያለፈ የመከራከሪያ ጉልበት የለውም። በተናጥል ባለቤትነት ተኮንኖ የወግ ማድመቂያ የሚደረገው ዐማራም ቢሆን የጋራ እንጂ፤ የብቻ አገር አለመገንባቱ ግላጭ የወጣ ሃቅ ነው። በርግጥም ኢትዮጵያ ያለፈችበት የታሪክ እርከኖች ጮኸው የሚመሰክሩት ጠጣሩ እውነት፣ ዐማራ የነበረው ሚና ከአገሪቱ ብሔራዊ ማዕቀፍ ዐውድ ተገንጥሎ ሊታይ አለመቻሉን ነው።

በዚህ ተጠየቅ፣ የሰሜኑን ጦርነት ተንተርሶ ከአዲስ አበባ እስከ ኋይት ሀውስ፣ ከአራት ኪሎ እስከ ካይሮ፣ ከካርቱም እስከ ቤልጄም፣ ከኢቢሲ እስከ ቢቢሲ… የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚፈተትበት መሰዊያ ላይ የቀረቡትን የወልቃይት እና ራያ ጥያቄዎች እንፈትሻለን።

የዛሬቱ ኢትዮጵያ፣ እንደ አገር ለመበጀት፣ ቢያንስ በሁለት የታሪክ እርከኖች ከማለፏ አኳያም፣ ከሀገረ- መንግሥቱ ኦሪት ዘፍጥረት መጀመሩ፣ ለነገረ-ዐውዱ ቅቡልነት አጋዥ ይሆናል።

፩ 

ቀዳሚው የ‹ብሔረ-ኢትዮጵያ› ግንባታ በጥንታዊው እና መካከለኛው የታሪክ ዘመናት ከመከናወኑ አኳያ፣ ልማዳዊውን የሀገር-ግንባታ መስመር መከተሉ ይታመናል። የዚህ ዋንኛ ትኳሬ ደግሞ የኢትዮጵያዊነትን ተፈጥሮ፣ ህልውና እና ራዕይ በመለኮታዊ ፍልስፍና መረዳትና መተርጉም በመሆኑ፤ ሃይማኖት የወቅቱ ልዕለ ኃይል ተደርጎ እንዲወሰድ አስገድዷል። በግርድፉ ከ“አክሱም”፣ “ዛጉዊ” እና “ሰሎሞናዊ ሥርዎ- መንግሥት” በተጨማሪ፤ “የሸዋ”ም ሆነ “የጎንደር” ተብለው የሚታወቁት የሥልጣኔ ዘመናት የከረረ ክርስቲያናዊ ባህሪ ቢኖራቸውም-ቅሉ፤ ከትግሬውም፣ ከዐማራውም፣ ከኦሮሞውም ተጋብቶ የተዋለደ እና በሥርዐቱ ውስጥ ኃይል ያከማቸ የትኛውም ቡድን የመንገሥ ዕድል ነበረው።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*