የወሎ የጭለማ እና የአርበኝነት ወራት | ከድር ታጁ

የአሁኑ የወሎ ግዛት፣ በሰሜን እና በደቡብ አስተዳደር ተከፍሏል። የሰሜን ወሎ ግዛት 48 ወረዳዎችን አካትቶ ይዟል። “ቆቦ” አንዱ ወረዳ ነው። አርባ የገጠር ቀበሌ አለው። ሀራ፣ አጋምሳ፣ ድቡስቃ፣ ዶቤ፣ ወርቄ፣ ቂልጡ፣ ሶዱ፣ አቢዩድ የተሰኙ ቀበሌዎች በቆቦ ወረዳ ሥር ናቸው። ከሐምሌ እስከ ጷግሜ 2013 ዓ.ም በእነዚህ ቀበሌዎች ላይ የጨለማ ወራት አልፈዋል። ልደትን የሚያስረግም ግፍ ተፈጽሟል። የወያኔን የጥፋት መርከብ የተሳፈሩ ኃይሎች ያለምንም ራሮት፣ ፍጡር-ከል ድርጊት እንዲነጥፍ አድርገዋል። መጻዔ ዕድላቸውን በማያውቁ ግፉአን ላይ የቅጽፈት በትራቸውን አሳርፈዋል። ንፁሀንን ቀጠፈዋል። የእምነት ተቋማትን፣ የሕዝብ ሀብት ንብረትን ዘርፈዋል፤ አውድመዋል።

ይኽ ጽሑፍ በእማኞች ምስክርነት፣ የ’ዚያን ሁነት ጥቂት ምስል ከስቶ ይዘግባል። ሁለት ተልዕኮ ይፈጽማል። የተከወነውን እና ዛሬም ድረስ ሊገታ ያልቻለውን የበላዔ- ሰባዊያኑን ድርጊት በቁንፅል ያሳያል፤ በእሣት ተፈትነው የፈነጠቁ ጽኑ ታጋዮችን ያስታውሳል። ለችግሩ መፍትሄ፣ ለጀግኖቹ ሥባሔ እንዲደርስ ይመኛል!

የወያኔ የጦር ወረራና የወሎ የሰቆቃ ገፆች

አቶ አሊ ሰይድ የወርቄ-ቂልጡ ተወላጅ ናቸው። 47 ዐመታቸው ነው። የወያኔ ጦር በዕለተ-ሰኞ ሐምሌ- 26-2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ወደ አካባቢው በድንገት ሲዘምት፣ እርሳቸው እዚያው ነበሩ። ህጻናቱና እንስቶቹ አካባቢውን ለቀው እንዲሸሹ አስተባብረዋል። እልህ አስጨራሽ ትግል መካሄዱን ያስታውሳሉ። 15 ታጋዮች መሰዋዕት መሆናቸውን፣ ከ80 በላይ የወራሪው ሠራዊት መውደቃቸውን፣ ቆየት ብሎ በደረሳቸው መረጃ አስደግፈው ያስረዳሉ። ሞላ መንገሻ እና በላይ መንገሻ የተባሉ አጎቶቻቸውን፣ ሮብሶ ሞላ የተባሉ እና እንደ አባት ያሳደጓቸውን አጎታቸውን ተነጥቀዋል። አቶ ተሾመ ጎብሳ የተባሉትን የአካባቢው ኗሪ፣ ታርደውና ተቆራርጠው ተገድለው ተመልክተዋቸዋል። ከ41-50 የሚደርሱ ቤቶች መቃጠላቸውን ይገምታሉ። ሦስቱ ጥንታዊ መስጊዶች ነበሩ። እያንዳንዱ አባ-ወራ ከ20- 30 የሚደርሱ ፍየሎች ነበሩት። በብዛት ከብትና ግመል ነው የሚያረቡት። ሁሉም የቃጠሎው ሰለባ ሆነው መቅረታቸውን ይናገራሉ።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*