የወያኔ እና የኤርትራ ፖሊሲው ተቃርኖ | ንብረት ገላው እና ሙሉዓለም ገ/መድኀን

የ1960ዎቹ የኢትዮጵያ አብዮት ንቅናቄ አንዱ ፍንካች፣ በትግራይ እና በኤርትራ የሽምቅ ወታደራዊ ባህሪ ይዞ የቀጠለው ትግል መሆኑ እሙን ነው። በርግጥ የትግራይ ዐመጽና ተቃውሞ መሪዎቹ ከሚሉትም ባለፈ፤ የመነሻ ምክንያቱ ሰፊና መዋቅራዊ ፍላጎት እንደነበረው አይዘነጋም።

በዚህ ዐውድ፣ የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎችን እና የትግራይ ልሂቃንን ተጣራሽ አቋምና ፖሊሲዎች በአጭሩ እንመለከታለን።

በትብብርና የቅራኔ ታሪክ የቆመው የወያኔ ፖሊሲ

ወያኔ አንድን አጋር ድርጅት ወይም ስብስብ ለወታደራዊም ሆነ ለፖለቲካዊ ፍላጎቱ ተጠቅሞ መጣልን ‹መርህ› በሚል የዳቦ ስም እንደሚያቆላምጠው ልብ ይሏል። እንዲህ ዐይነቱን ኀቡዕ ምንፍቅና የተጫነው “ግንኙነት”ም፣ ከበርካታ ድርጅቶች ጋር እንዳደረገው ሁሉ፤ ከኤርትራ ዐማጺያንም ጋር ሲዳከም ትብብርን፣ ሲጠናከር ቅራኔን የተከተለ “ወዳጅነት” ፈጥሮ ነበር። በተለይ በትግሉ መጀመሪያ አካባቢ በአስመራ ዩኒቨርሲቲ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ከኤርትራው ነፃ አውጪ ጀብሓ የድጋፍ ቃል እንዲገባላቸው ብዙ ጥረዋል። በኋላ ምንም እንኳ ጀብሓን ጥለው ሻዕቢያ ላይ ቢንጠላጠሉም። ይህን በተመለከተ ጆን ያንግ “The Tigray and Eritrean Peoples Liberation Fronts;- A History of Tensions and Pragmatism” (1996) የሚል ርዕስ በሰጠው ጽሑፉ ሻዕቢያ፣ ለወያኔ ድጋፍ የማድረግና የማጠናከር ውሳኔ ላይ የደረሰው፣ የነፃነት ጥያቄውን መቀበሉን መሰረት በማድረግ እንደነበረ አስረግጧል።

በቀጣይነትም የወያኔ የጦር አዛዥ ስዬ አብርሃን ጨምሮ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉት የአመራር ቡድን፣ በኤርትራ ለሦስት ወራት ስልጠናዎችን ወስዶ ተመልሷል። አስመራ በነበሩ የትግራይ ተማሪዎች የድጋፍ ቃል ሲጠየቅ የነበረው ጀብሓም፣ ትግራይ በነበረው የመንግሥት ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ከሰነዘራቸው ጥቃቶች፣ ወያኔ የውጊያ ልምድ ማግኘቱ አይካድም። ይህም፣ በጀብሓ እና ወያኔ መሃል በጎ ወታደራዊ ትብብር እንዲፈጥር ያስቻለ ነበር። በተለይ ደርግ በ1968 ዓ.ም (በፈረንጆቹ 1976) የኤርትራ ዐማጺያኖችን ለመምታት “ራዛ ኦፕሬሽን” የተሰኘ ዘመቻ ባወጀበት ወቅት፣ ወታደራዊ ትብብሩን ሻዕቢያም ተቀላቅሎት፣ ዘመቻውን አክሸፈውታል።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*