የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል አስፈላጊነትና ተልዕኮዎቹ | ኤርምያስ ለገሰ

መንደርደሪያ፣

አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አንድ ዐመት የጦርነት አዙሪት ውስጥ ገብታ፣ የሕልውና አደጋ አጋጥሟታል። ተወደደም ተጠላ፣ የኢሕአዴግ ፍንካች የሆኑት ሕወሓት እና ብልጽግና የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ጦርነት ውስጥ ከተውናል። በዚህ ምክንያት ወዴት ነው የምንሄደው? ኢትዮጵያንስ ምን ልናደርጋት ነው የተዘጋጀነው? የዐማራን ማኀበረሰብስ ወዴት ነው ልናደርሰው የምንፈልገው? የሚሉት ጥያቄዎች በስፋት እየቀረቡ ነው።

በሌላ በኩል፣ የዐማራ ማኀበረሰብ ሁሉን አቀናጅቶ የሚያንቀሳቅስ አመራር በማጣቱ ቀውስ በዝቶበታል። ይህም፣ ሁሉን ዐቀፍ ሕጋዊ አደረጃጀት በጊዜ የለንም እሳቤ መፍጠር ካልተቻለ፣ ችግሩን ከድጡ ወደማጡ ማድረጉ አይቀሬ ነው። አሁን ካሉት ሕጋዊ አማራጮች ውስጥ፣ ሁሉንም የሚያካትት የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል ማቋቋሙ ቅድሚያ የሚሰጠው ይመስለኛል። እርግጥ እንዲህ ዐይነት ኃይል ይቋቋም ሲባል፣ ከተጨባጩ ሁኔታ አንጻር በጣም ከባድ መሆኑ አያጠያይቅም። በተለይ ከገዥው ፓርቲ ብልጽግና የሚነሳው አቧራ በቀላሉ የሚራገፍ አለመሆኑ ተገማች ነው። ያጋጠመውን ከፍተኛ የቅቡልነት ውድቀት ለመሸፋፈን የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት እርምጃ እስከ መውሰድ ሊሄድ ይችላል።

ይህም ሆኖ፣ “ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም” እንደሚባለው፤ ዐማራ ያጋጠመውን ነባራዊና ሁሉንተናዊ ችግሮች ለመፍታት ከሕዝባዊ ኃይል ውጪ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም። የሚመሰረተው ሕዝባዊ ኃይልም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ በመሆኑ፣ ሄዶ ሄዶ የጋራ ድልን ማረጋገጡ አይቀርም።

ከዚህ አኳያም፣ ምን ዐይነት ሕዝባዊ ኃይል መመስረት እንደሚገባው የመነሻ ሃሳብ አቀርባለሁ። በተለይ የዐማራ ሕዝብ የህልውና አደጋና የኃይል አሰላለፍ፣ የእቅዱ ታሳቢዎች፣ የሕዝባዊ ኃይሉ አቋሞችና እምነቶች፣ የሽግግር መንግሥቱ ዓላማዎች፣ ግቦችና አደረጃጀቶች፤ እንዲሁም እቅዱ የሚፈፀምበት አቅጣጫዎችንም ለማመላከት እሞክራለሁ።

  1. የዐማራ ሕዝብ የህልውና አደጋና የኃይል አሰላለፍ ፣

1.1. ሕወሓት እና ወታደራዊ ኃይሉ፣

የዐማራ ሕዝብ የሕልውና አደጋ በመጀመሪያ የሚመነጨው ከሽብርተኛው የሕወሓት ቡድን እና ወታደራዊ ክንፉ ነው። ጦርነቱ በተከፈተ ሰሞን የፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራሮቹ “ዋነኛ ጠላታችን የዐማራ ልሂቃን ነው” የሚል ዛቻ አስተላልፈው እንደነበረ ይታወሳል። ይህ ዛቻም፣ አንድ ማኀበረሰብ ያለ ልሂቃኑ ማዕዘን የሌለው ቤት እንደሚሆነው ሁሉ፤ መላውን ዐማራ ለማጥፋት የተቃጣ ጥቃት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*