የጄነራሉ ምስጢሮች – (ከብ/ጄ ተፈራ ማሞ ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ)

የዐማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ፣ ባለፈው ሳምንት በድንገት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ፣ ከ“ፍትሕ መጽሔት” ጋር ሰፊ ቃለ-መጠይቅ አድርገዋል። ጄነራሉ፣ በልዩ ኃይሉ ላይ ‹እየተፈጸመ ነው› ያሉትን ደባ ጨምሮ፤ በቀጣይ ወልቃይትና ራያን ለሕወሓት እስከ መስጠት የደፈረ ሴራ ሊከሰት እንደሚችል ዘርዝረዋል። በጦርነቱም መከላከያ ኃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣቱን ይጠቅሳሉ። መልካም ንባብ።

ጄነራል ወደ ዐማራ ልዩ ኃይል አዛዥነት በድጋሚ መቼና እንዴት ተመለሱ?

የተመለስኩት 2013 ዓ.ም ሐምሌ መ መሪያ ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ የክልሉ መንግሥት የክተት ጥሪ በማስተላለፉ፣ እኔም እንደ ዐማራነቴ ጠላት በህልውናዬ ላይ የመጣ በመሆኑ ነው። በነገራችን ላይ፣ ጥሪውን ተቀብለን ለመግባት ስንጣደፍ፣ “ለምን ትገባላችሁ? ጦርነቱን ሕወሓት ማሸነፉ አይቀርም?!” የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ።

ከአመራሩ መሃል ነው?

ከአመራሩም ከጄነራል መኮንኖችም ‹ሕወሓትን የሚያቆመው ኃይል የለም› በሚል አንዳንድ ወጣ-ያሉ ነበሩ። በዚህ ላይ፣ የአዴፓ አመራር በፊት በእኛ ላይ ጤናማ አመለካከት ስለሌለው፣ እንዳንመለስ የነበረውን ፍላጎት በማስታወስ ነው ‹ባትገቡበትስ?› ሲሉ የመከሩን። በወቅቱ መከላከያ ሠራዊቱ የያዘውን ቦታ እየለቀቀ ወደኋላ እየመጣ ነበር። በርግጥ፣ ጄነራሎቹ ከፊት፣ ጦሩ ከኋላ እየተናደ መሆኑ፣ ትንሽ እንግዳ ክስተት ነበር። እነሱም ይሄንን እየጠቀሱ ነው ‹መከላከያ እየመከተው አይደለም› ይሉን የነበረው። ‹አይ ግዴለም! አማራጭ የለንም። የምንገባውም ለአመራሩ ሳይሆን፤ እየተመታ ላለው ሕዝብ የዐቅማችንን ለማድረግ ነው። መሞት ካለብንም እንሞታለን እንጂ፤ ጥሪውን እንቀበላለን፤› ብለን ገባን።

ስንት ናችሁ አብራችሁ የገባችሁት?

ከእኔ ጋር ስድስት ነን። ጄነራል አበራ፣ ጄነራል ባዩ፣ ጄነራል ዘውዱ፣ ጄነራል መሰለ ወይም (ጎበና) እና ጄነራል ማሞ። በአንድ ላይ እንደገባንም የመመሪያ ሥራ ያደረግነው፣ አጠቃላይ ልዩ ኃይሉን ማዋቀር በመሆኑ፣ ምልሱንና የነበረውን አሰባስበን አደራ ነው።

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*