የፖለቲካ ፓርቲዎች ርዕዮተ-ዓለማዊ አሰላለፍ | ዮሴፍ ጣሰው ታደሰ

ኢትዮጵያችን ከውስጣዊ የመንግሥት አመራር (Ruling establishment) ለውጥ በኋላ፣ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ባለፈው ሰኞ ማካሔዷ ይታወቃል። ይህ ምርጫ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ካለፈው ዐመት ወደ ዘንድሮ ከተዘዋወረ በኋላ፣ ግንቦት 28/2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረ ቢሆንም፤ በተለያዩ አስተዳደራዊ ምክንያቶች በድጋሚ ተራዝሞ፣ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በ443 የምርጫ ክልሎች ተካሔዷል። ከትግራይ ውጪ ላሉ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞለታል።

ይህንን ምርጫ ተጠባቂ ያደረገው ብዙ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ይመልሳል በሚል ብቻ ሳይሆን፤ በርካታ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ከማስነሳቱ እና በድኀረ-ምርጫው ሊፈጥር የሚችለውን ለውጦች እና ውዝቦችንም ታሳቢ አድርጎ ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ማግለላቸው፤ ሌሎች ደግሞ ምርጫው “መሠረታዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ ነው” የሚል መግለጫ ማወጣታቸው (Ethiopia Insid­er)፣ ከታዋቂ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች መታሰር ጋር ተደምሮ፣ የምርጫውን ፍትሐዊነት እና ቅቡልነት (legitimacy) ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።

ይህም ሆኖ፣ የጠቅላላ ምርጫው ውጤት የተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮችን በተመለከት “አናሳ” የማይባል ለውጥ ይዞ ሊመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የክልል እና የፌደራል መንግሥታት የሥልጣን ክፍፍል ጉዳይ፣ የብሔር ብሔረሰቦች የራስን በራስ የማስተዳደር፤ እንዲሁም የ‹ክልል እንሁን› እና የብሔር ጥያቄዎችን ከአገራዊ አንድነት ጋር የማጣጣም ጉዳይ፣የኢኮኖሚ እና የትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና የመሳሰሉት አንገብጋቢ አጀንዳዎች፣ በዚህ ምርጫ በሰፊው ከተዳሰሱ ወሳኝ ጥያቄዎች መካከል ይገኙበታል። ….

Continue Reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*