ዳዊት ታደሰ | ዘመነ-ተረት

ከሰሞነኛው የጎንደር ክስተት እንጀምር። በውግዘት ብቻ የማይታለፈው አሳፋሪው ድርጊት ተፈጸመና እንደተለመደው አገር በድጋሚ ማቅ ለበሰች። በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ መስጠት የሚገባቸው የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት በረዥም ዝምታ ተዋጡ። የጸጥታ ኃይሎችም እንደስማቸው ጸጥ

እንዳሉ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው በድንገት ብቅ ብለው፣ ለፍቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በሲዳምኛ ቋንቋ አስተላለፉ። በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከተሰማ ከ48 ሰዓታት በኋላ ደግሞ፣ አንድ አጠር ያለች መጣጥፍ በዚሁ ገጻቸው አስፍረዋል። ስለጎንደሩ ጉዳይ የጻፉት እንደሆነ በመገመት በርካቶች ሲወያዩበት ነበር። ምናልባት፣ “አጥፊውን አውግዘን ከተጠቂው ጋር እንቆማለን እንጂ፣ ጥፋቱን በሌላ ጥፋት ለማባባስ መሞከር የለብንም፣” የምትለው ሐረግ ካልሆነች በቀር፤ ድርጊቱን የሚኮንን ወይም የሟች ቤተሰቦችን የሚያጽናና

ወይንም በአጥፊዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን የሚገልጽ ምንም ፍንጭ አልሰጡም።

የተረት አባት

 የግብፁ አልሲሲ ለአገሬው ቃል መግባት አይታክተውም። ከሦስት ዐመት በፊት “እንመካከር” በሚል መሪ ቃል ወጣቶች በአገራቸው ጉዳይ የሚወያዩበት መድረክ እንዲዘጋጅ ላይ ታች ሲል ነበር። ‹የምሩን ነው› ብለው ያሰቡት የምስር ልጆች፣ ሥራቸውን ሲጀምሩ ግን የጠበቃቸው እስር ሆነ። የገማል አብደልናስር ታሪክም እንደዚሁ ነው። በአማላይ ዲስኩሩ የወቅቱን ትውልድ አስክሮት ነበር። አጠቃላይ የአገዛዝ ዘመኑ ሲገመገም ግን ከሠራው ይልቅ፣ የካደው ሚዛን ይደፋል። ኦሪታዊ አገራት በዚህ ይመሳሰላሉ። የተረት ክምችታቸው በርከት ስለሚል ነው መሰል፣ የተረት አባቶች አያጡም።

እኛም ጋር የሆነው ይኸው ነው።

እርሳቸው፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ወደሥልጣን እንደወጡ ቃል የገቡልን ታላቅ አገር እንደሚመሰርቱ ነበር። የወላለቀ ሥርዐት ተረክበው

የተዋጣለት ግዛት በአይናችን ሊያሳዩን እንደሚችሉ አሳመኑን። አሁን ባለው ሁኔታ፣ እንኳን የተዋጣለት ግዛት፣ የወላለቀው ሥርዐትም ቅንጦት ሆኖብናል። ‹የኢትዮጵያን ችግር ይፈታሉ› የተባሉት ሰው ራሳቸው ችግር ሆኑ። እንደ መሲህ ቢመሰሉም፣ መሠረታዊ የአገር ማስተዳደር ዘይቤ ባለማወቃቸው አገራችንን ለጎበዝ አለቆች መጫወቻነት አሳልፈው ሰጡ። …

 

Continue reading

 

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*