ፋሽዝም በአዲስ አበባ | ጌጥዬ ያለው (የህሊና እስረኛ)

ያኔ ከደደቢት በረሃ ተምዘግዝጎ እምዬ ምንሊክ ቤተ-መንግሥት ሲገባ፣ ከእነ ዋለልኝ መኮንን እና ምዕራባዊ ጌቶቹ የተማረውን ሰው ጠል እና ሰው ፈጅ ፖለቲካ ለማዋቀርም ሆነ የተለያዩ ብሔሮችን የሚወክሉ ዘረኛ ፓርቲዎችን እንደ ችግኝ ማፍላቱ ጊዜ አልፈጀበትም። ለዚህ ደግሞ፣ አስቀድሞ በግንባር ስም የመሰረተው፣ ነገር ግን በሕወሓት የበላይነት የሚዘወረው ኢሕአዴግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በዚህ ወቅትም ነው፣ የትግራዩ ቡድን ‹ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ያገናኘኛል› በሚል ተስፋ ባልንጀራ አድርጎት ከነበረው ኦነግ ጋር፣ በጠመንጃ የሚፈላለግ ባላጋራ የሆነው። ይሁንና፣ እነ መለስ ዜናዊ “ሁለት ባላ ትከል፤ አንዱ ሲሰበር፣ በአንዱ ተንጠላጠል፤” በሚለው ነባር መርሃቸው መሰረት፣ በ1982 ዓ.ም ከተለያዩ ፓርቲዎች እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረጓቸው ውጊያዎች የማረኳቸውን ጨምሮ፤ በሻዕቢያ የምርኮኛ ካምፕ ታስረው የነበሩትን ኦሮሞ ወታደሮች አሰባስበው፣ መጀመሪያ በኢሕዴን ስር እንዲዋጉ ካደረጉ በኋላ፤ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ “የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ)” የተሰኘ ተለጣፊ የፖለቲካ ቡድን የዐማራ አፅመ ርስት በሆነችው የሸዋ ደራ ከተማ ላይ እንዲመሰረቱ አድርገዋል።

እንግዲህ፣ ይህ የምርኮኞች ስብስብ እርሾ የሆነው ድርጅት ነው፣ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ጠልፎ በብልፅግና ስም ፍፁማዊ የሥልጣን  በላይነት የያዘው። በርግጥ፣ በዚህ አቋራጭ መንገድ ሾልኩ አራት ኪሎን እንዲጠቀልል የብአዴን አስተዋፅኦም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ በገሃድ ይታወቃል። መቼም፣ ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ኃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዱ ሥልጣን መልቀቁን ተከትሎ፣ ለኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርነት በተደረገው ምርጫ፣ የብአዴን ሊቀ-መንበር ደመቀ መኮንን ከውድድሩ ራሱን አግልሎ፣ የኢሕዴዱ ሊቀ-መንበር ዐቢይ አህመድ እንዲሚረጥ ማድረጉን ራሳቸው በሚዲያ ተናገሩት ሃቅ ነው።

 Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*