ከአሜሪካ ጋር የተጀመረው ጠብ ሰሞኑን ከምታዩት ደረጃ ላይ ደርሶዋል። በማእቀብ እና በእርዳታ ክልከላ የታጀበው ጫና በሚያስገርም የሚዲያና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተመራ ቀጥሏል። ያው አንባቢ ሆይ፡- እንደምታውቀው፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ አይመቹኝም። ከሕወሓት ጋር ባላቸው ዝምድናም ይሁን፤ ዓለም ላይ ባላቸው ሚና ክፉኛ ከሚታዘቧቸው አንዱ ነኝ። ስለሴራዎቻቸውና ስለፍላጎቶቻቸው የሚሰማኝን ነገር ያላልኩበት ጊዜ የለም። ከ10 ወራት በፊት “ዐቢቺኒያ” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። አገራችን በቻይና እና በአሜሪካ መካከል በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ሊያጋጥሟት የሚችሉ ፈተናዎችን ለመገመት የሞከርኩበት ነበር። “መሬት ንሳ” በሚለው የጽሑፉ ክፍልም፣ የማእድንን ጉዳይ አንስቼ ነበር። ከሁለት ወራት በፊት ተመሳሳይ ምልከታ ገጠመኝ። “ሩሲ” ከተባለ የመረጃ ምንጭ ላይ የቀረበው ጽሑፍ የማእድኑን ፖለቲካ ሰብሰብ ባለ መልኩ አስፍሮት አገኘሁ። የትግራዩን ጉዳይ “Ethiopia: A New Proxy Battlespace? “በሚል ርዕስ፣ Proffessor Ann M. Fitz-Gerald ከማእድን ፖለቲካ ጋር አያይዘውታል። አሜሪካንን፣ ከሕወሓት ጎን እንድትቆም ያደረጋት የ“ዐረቢያን ኑቢያን ሺልድ ነው” የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ “የኢኮኖሚን ነገር ከብሔራዊ ደህንነት ጋር ለሚያመሳስለው የባይደን መንግሥት፣ የትግራዩ ጦርነት ቻይናን የመምቻ አንዱ ፕሮጀክት ነው።”
ለመሆኑ ዐረቢያን ኑቢያን ሺልድ ምንድነው? ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅምስ ጋር ምን ያያይዘዋል? ለቻይና እና ሩሲያስ ምናቸው ነው? አሜሪካና ሰሞነኛ ወዳጇ ሕወሓትስ ቀጣይ አቅጣጫቸው ወዴት ሊሆን ይችላል?

“ዐረቢያን ኑቢያን ሺልድ”
በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚታወቅ የማእድን ቀጣና ነው። ዓለም፣ በተለይም አሜሪካ በአንገብጋቢ ሁኔታ የምትፈልጋቸውን የማእድን አይነቶች አከማችቶ ይዟል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ግብጽና፣ ምዕራባዊ ገልፍ ድረስ ይዘረጋል። የኤርትራን 65 ከመቶ ይሸፍናል። በኢትዮያ ደግሞ፡- በትግራይ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላና በቤንሻንጉል፤ እንዲሁም በዐማራ ውስን አካባቢዎችን ያካልላል። ወርቅ፣ ሲልቨር፣ ኮፐር፣ ዚንክ፣ ፖታሽ… ወዘተ እንደልብ ይገኙበታል። ሁሉም በኢነርጂው፣ በወታደራዊውና በማኑፋክቸሪንጉ ዘርፍ እንደ ኦክስጅን የሚፈለጉ ናቸው። ካርታው ላይ ትንሽ ደብዘዝ ብሎ የሚታየው የኤርትራውንና የትግራዩን የዐረቢያን ሺልድ አካባቢዎች የሚጠቁም ሲሆን፤ በአንድ ድርጅት ስር የተያዙ ሦስት የማእድን ሳይቶችን ያመለክታል። የጽሑፌ ማጠንጠኛ በመሆኑ እዚያው አካባቢ እንቆይ።
Be the first to comment