
ትግራይ ክልል፣ ምዕራባዊ ዞን፣ ወልቃይት ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ወደ ግል ይዘዋወራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፋብሪካዎች አንዱ መሆኑን ተከትሎ የትግራይ ንግድ እና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤት ሀብት በማሰባሰብ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አሰፋ ኃይለ ሥላሴ እንደተናገሩት፣ የአዋጪነት ጥናት በምክር ቤቱ ተጠንቶ በመጠናቀቁ የክልሉን ምሁራን፣ ባለሀብቶች እና በውጪ የሚኖሩ ዳያስፖራዎችን በማሳተፍ እና ሀብት በማሰባሰብ ጨረታውን ለማሸነፍ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። ይህንን እቅድ ምክር ቤቱ ይፋ ካደረገ ገና አንድ ሳምንቱ መሆኑን የገለፁት አቶ አሰፋ፣ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ግን ከፍተኛ ፍላጎቶች መምጣታቸውን ገልፀዋል።
መንግስት የተለያዩ ድርጅቶችን ለግል ባለሀብቶች ለማዞር እቅድ እንዳለው ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ ግዙፍ የመንግስት እና የልማት ድርጅቶች ለመዘዋወር ጊዜ እየጠበቁ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከል የወልቃይት የስኳር ፋብሪካም አንዱ ነው። ፋብሪካው በመጨረሻ በማን ይጠቀለል ይሆን? የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነው።
በ2004 ዓ.ም የተጀመረው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ 71 በመቶ መድረሱ በቅርቡ መገለጹ የሚታወስ ነው። ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል የሆነው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ወደ ግል ይዘዋወራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፋብሪካዎች መካከል አንዱ ነው። ፋብሪካው እስካሁን ለ1ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ከ50- 60 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ ኣስኪያጅ ኣቶ ኣመናይ መስፍን እንደተናገሩት ግንባታው ከሶስት ኣመት በፊት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ተጀምሮ የነበረ ሲሆን ይሁን እንጂ የበጀት እጥረት ኣጋጥሞት ሳይገነባ የቆየ አንደኛ ምዕራፍ በኣሁኑ ግዜ ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር በተደረገው በረጅም ግዜ የሚከፈል የብድር ውል በ10 ነጥብ ኣምስት ቢልዮን ብር ግንባታው እንደተጀመረ አስታውሰዋል። በኣሁኑ ግዜ የፋብሪካ ግንባታ የሚያከናውነው የቻይና ኩባንያ ለግንባታው አስፈላጊ የሚባሉ መሳርያዎች በማስገባት የመኖርያ ቤቶች ግንባታና ፋብሪካው የሚያርፈው ቦታ የጠረጋ /ሳይት ክሊራንስ/ ስራዎች መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል። አቶ አመናይ ጨምረውም አጠቃላይ የፋብሪካው ዲዛይን ተጠናቆ ከስኳር ኮርፖሬሽን ስምምነት እንደተደረሰና ቀደም ሲል በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ተጀምረው የነበሩ ስራዎች አሁን ለግንባታው ሙሉ ለሙሉ የያዘው የቻይና ኩባንያ እንዳስተላለፈም ተናግረዋል።
የፈረንሳይ ኩባንያ በአማካሪነት፣ የቻይናና የውስጥ ኣገር ኩባንያዎች ደግሞ የፋብሪካ ግንባታና የመሬት ስራዎች /ኧርዝ ዎርክ/ በማሳተፍ የሚገኘው ኣንደኛ ምዕራፍ የፋብሪካ ግንባታ ሙሉ በሙሉ በሁለት አመታት ውስጥ እንደሚያልቅ ጠቁመዋል። በ2011 ዓ.ም ኣጋማሽ በቃሌማ ግድብ የሚለማው 3 ሺህ ሄክታር መሬትና በእስራኤል ኩባንያ በ4 ቢልዮን ብር በጀት የተከዜ ወንዝ በመጥለፍ 7 ሺ ሄክታር መሬት የጠብጠብታ መስኖ በኣጠቃላይ በ10 ሺህ ሄክታር መሬት በሚለማ የሽንኮራ ኣገዳ ልማት ፋብሪካው ስራውን እንዲጀምር ተደርጓል። ሁለተኛ ምዕራፍ የፋብሪካ ግንባታም ጎን ለጎን እንዲከናወን መደረጉንም ጨምረው አነስተዋል። የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ማለትም ኣንደኛ እና ሁለተኛ ምዕራፍ ፋብሪካዎቹ ስራ ሲጀምሩ በኣመት ኣራት ሚልዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር፣ 41ሺ 654ሜ3 3 ኢታኖል፣ ከ80 እስከ 100 ሺ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠርና 120 ሜጋ ዋት ሃይል በማመንጨት 60 ሜጋ ዋት ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪው 60 ሜጋ ዋት ደግሞ ወደ ብሄራዊ የሃይል ቋት እንዲያስገባ ይጠበቃል። በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ለአጠቃላይ ግንባታ 50 ቢሊየን ብር ተመደቦለታል። ይህ ፕሮጀክት ከመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ጎን ለጎን የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታውም እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። ፋብሪካው በአንድ ቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይም የመጀመሪያውን ምዕራፍ የምርት ሙከራ ሂደት አከናውኗል።
በአሁኑ ወቅት ለፋብሪካው ግብዓት የሚሆን የአገዳ ምርት የማልማት ሂደት የሚያስችል 50 ሺህ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የፕሮጀክቱ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀይለ ገብረመድህን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮንስትራክሽን እና በብሩህ ተስፋ ግንባታው ሲካሄድ የነበረው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ፣ በአሁኑ ወቅት በቻይናዊው ድርጅት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። ከፋብሪካ ግንባታው ጎን ለጎንም የማሽነሪ ተከላ እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ ሀይለ ተናግረዋል።
ውጭ አገር ለሚኖሩት ትክክለኛ መፍትሔ ነው በዚው ቀጥሉ ፍትህ ፍትህ 💪💪💪💪💪💪