ተፈናቃዮችን ማን ይድረስላቸው?

ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ላለፉት ሦስት ዓመታት በከባድ የፀጥታ ችግር ውስጥ ቆይቷል። አሁንም ከዚህ የፈተና አዙሪት ውስጥ መውጣት አለመቻሉን ከስፍራው የሚወጡ ዜናዎች ጠቋሚ ናቸው። ክልሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚካሄድበት መሆኑ የውጭ ኃይሎችንም ትኩረት ስቧል። አገሪቱ የራሷን ሀብት ጥቅም ላይ ላውል ብላ ስትነሳ የተነሱ ጠላቶቿ ብዙ እየሆኑ መጥተዋል።

በድንበር በኩል የተፈጠረው ግጭት ጉልህ ማሳያ ነው። የሱዳን እና የግብፅ ፖለቲካዊ ሴራ መልኩን እየቀያየረ ነው። ለድርድር ቢቀመጡም አይስማሙም። ከለውጡ ወዲህ እንኳን ከአፍሪካ እስከ አውሮፓ አደራዳሪዎች ያልተቀመጡበት ወቅት የለም። ለውይይት በሄዱ ቁጥር ተቃራኒ ጉዳይ ይዘው ነው። አገራቱም በተቃራኒ ለቆሙት ይተባባራሉ። ኢትዮጵያ ተስፋ እንድትቆርጥ ዙሪያ ጥምጥም ይሰራሉ።

መተከል ዞን ከላይ የተጠቀሰው ሴራ ነፀብራቅ ነው። ፖለቲካዊ ዓላማውን ለማሳካት ከቴሄደባቸው መንገዶች ውስጥ ዘር ተኮር ጥቃት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህ ዓላማ ተባባሪዎች ከሕወሓት እና ሸኔ በተጨማሪ ከክልሉ የለውጥ አመራሮች እስከ ፌደራል መንግሥት ድረስ መኖራቸው ይነገራል። በዞኑ ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የሚባሉ የዐማራ ብሔር ተወላጆች የጥቃቱ ዋነኛ ሰለባ ሆነዋል። ከብዙ መፈናቀል እና ግድያ በኋላ ከጥቃት የተረፉትን ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*