ተገልሎ የቆየው የዐማራ ፖለቲካ እና አሁናዊ ፈተናዎቹ | ዳንዔል ተፈራ ጀ.

እየውልህ ወንድማለም፣ ስለ ዐማራ ስጽፍልህ መስከንተሪያ ያስፈልገዋል። መንደርደሪያ በለው። ወደኋላ ትሄድና ወደፊት ትንደረደራለህ። በጥንቃቄ። ዐማራ ስለሚባል ሕዝብ እና ፖለቲካው ስታነሳ ወደኋላ በጣም ሄደህ ካልተንደረደርክ፣ ወደፊት አርዝመህ ለማየት እጅግ ይቸግርሃል። ከስር ከመሰረቱ ካልጀመርከው፣ ነገርህ ኹሉ አሸዋ ላይ እንደተሠራ ድንኳን ይሆንና፤ አውሎው ነፋስ ሲመጣ ብትንትኑን ያወጣብሃል። እናም፣ ወደፊትህ የምትመለከተው ያጥርና፤ ከራስህ ጋር ጭምር መግባባት ይሳንሃል። የኋላው ከሌለ የወደፊቱም የለም። ማስከንተሪያ ያስፈለገበት ዋናው መነሻም ይኼው ነው።

በዚህ ላይ፣ የዐማራ ፖለቲካ ስልክህን ከኪስህ አውጥተህ፣ ቡናህን እየጠጣህ ‹ማርክ ዙከርበርግ› በዘረጋው የፌስቡክ ሜዳ ላይ በሁለት አንቀጾች ጫርጫር አድርገህ የምትበትነው ጥሬ አይደለም። በጣም ወደኋላ ሄደህ፣ የሀገረ-መንግሥት ምስረታ እና የኢትዮጵያን አፈጣጠር መርምረህ፣ የሕዝቡን በጎ መዋጮ ፈትሽ የምታገኘው ሃቅ አለና።

በርግጥ፣ በዚች መስከንተሪያ ጠርንፌህ፣ ወደኋላ ብዙ የማራቅ ፍላጎት የለኝም። ዳሩ፣ ላድርገውስ ብል በምን ዐቅሜ?! ባይሆን ትንሽ ላንደረድርህ። የቅርቡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቁልቁለት ስለሚበዛው እንድርድሮሹ ላይ ካልተጠነቀቅን፣ አደጋው የበዛ ነው። የጽሑፉ ዓላማም የዐማራ ሕዝብ ላይ እንደ ጅብራ የተገተረውንና አልረጋ ያለውን አሁናዊ ፖለቲካ በስሱ መፈተሽ በመሆኑም፣ ሩቅ አልወስድህም።

ውድ አንባቢ ሆይ! በዚህ ተጠየቅ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ያልተጠቀሱት ትኩረታችን ዐማራ ላይ ብቻ ከመሆኑ አኳያ እንደሆነ ልብ ትልልኝ ዘንዳ በአክብሮት አሳስባለሁ።

አሁን ወደ ርዕሰ ጉዳያችን እንለፍ።

Continue reading … 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*