ፍትሕ እና አገር ዐቀፍ ውይይት | ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ገሮች እና መንግሥታት ቀውስ ላይ የሚወድቁት ፍትሕ ሲጠፋ ነው:: ፍትሕ፣ ነፃነትና ወንጀለኞችን መቅጫ እንጂ፤ የሕዝብ መጨቆኛ መሳሪያ አይደለም:: ፍትሕ ለሁሉም እኩል ናት:: ፍትሕ በነፃነት መናገርና መደመጥ፣ በደልን ማጥፋት፣ የሕዝብን አንድነትና ሰላም መጠበቅ ማለት ነው:: ፍትሕ ለመሪዎች ስትገብር ግን፣ የአገር አንድነት ምሶሶ የሆነው የሕዝብ የበላይነት ይናዳል። መድህን መሆንዋም ቀርቶ፣ የጨቆኞች መሳሪያ ትሆናለች:: ይህንን ሚዛን የሚያስጠብቀው ሕዝባዊ ሕገ-መንግሥትና ምርጫ ነው:: ሕግ አውጪውም፣ ፍርድ ሰጪውም፣ ሕግ አስፈፃሚውም በግልፅም ሆነ በተሸፋፈነ መልክ በአንድ ወይም በጥቂቶች እጅ ስትወድቅ፣ የአገር መፈራረስንና የሕዝብ እልቂትን ያስከትላል:: ሦስቱ ክፍሎች ተለያይተው በፍፁም ነፃነት ሕዝብ በመረጠው ሕገ- መንግሥት ሊሠሩ እንዲችሉ፣ ምን ዐይነት ሕዝባዊ ጉባኤ ሊደረግ እንደሚገባው በዚህች ጽሑፍ ለአንባቢዎች አቀርባለሁ::

ቀጪ ፍትሕ (RETRIBUTIVE JUSTICE)

ያለ ሰላምና ፍትሕ መረጋጋት ሊኖር አይችልም። የማንኛውም አገር ዐቀፍ ውይይት ዓላማ ወደ ሰላምና መረጋጋት የሚደረግ ሽግግር መሆን አለበት። ይህን ለማሳካት ብቸኛው መሣሪያ ፍትሕ ብቻ ነው። ፍትሕ መኖር አለበት፤ የጥላቻ አይዲዮሎጂ የሚያስተዋውቁ ሰዎች ከቅጣት ማምለጥ አይችሉም። በአገሪቱ ለደረሰው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር እልቂትና ዘረፋ ኃላፊነት አለባቸው። የእነዚህ ወንጀሎች ፈፃሚዎች ለፍርድ ቀርበው፣ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ መቀጣት አለባቸው። እነዚህ ችሎቶችና የጥፋተኝነት (የቅጣት) ውሣኔዎች ብዙውን ጊዜ የተጠቀሱትን ጥፋቶች ለመፈፀም የተባበሩትን በማስቀጣት ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን፤ የሽግግርና የመልሶ ማቋቋም ፍትሕ ግን በተጐጂዎች ፍላጐቶች፣ በግጭት መሠረታዊ መንስኤዎች እና ጥፋተኞችን ከሕብረተሰቡ ጋር በማቀላቀል መልሶ ለማቋቋም በሚቻልበት እድል ላይ ያተኩራል። የዚህ ዐይነቱ ፍትሕ ጽንሰ-ሃሳብ ወንጀል በድጋሚ እንዳይፈፀም ለመከላከል፣ ጥፋተኞችን ለመቅጣትና መልሶ ለማቋቋም፤ እንዲሁም ሰዎች በሰላም አብሮ መኖርን እንዲማሩ ማድረግ ነው።

የመጨረሻ ዓላማው የሚከተሉትን ይጨምራል፡- የሕጋዊነትን እሴትና የሕግ የበላይነትን ማስፋፋት እና ጉዳዩን መዝጋት። ተጐጂዎችና ወንጀለኞች ከተስማሙ እውነቱን ሙሉ በሙሉ ለማግኘትና እርቅ ለመጀመር ውይይት ማነሳሳት ይችላሉ። ለራሷ ሰላም ያለባት አገር ለመፍጠር፣ በአንድነትና በሕብረት ወደፊት ለመንቀሳቀስ እና ለማንኛውም ሌላ አማራጭ ፍትሕ መቅደም አለበት። የሕግ የበላይነት በሌለበት፣ አገር አይኖርም። ማንኛውም ዜጋ ለማፍቀርና ለመታረቅ ሊገደድ አይችልም። የግል ምርጫዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን፣ የሕግ የበላይነት በፍቅር፣ በይቅርታና በእርቅ በማያምኑ ሰዎች፣ ሌሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥበቃ ያደርጋል።

«ይቅር ባይነት ማለት ልባዊና ስለሆነው ነገር መግባባት ላይ የሚደረስበት፤ እንዲሁም የደህንነት ስሜት የሚዳብርበት እና ጥላቻ የሚወገድበት (ከሁሉም በላይ እንዴት ይቅር ማለት እንደሚቻል የሚታወቅበት) የውስጥ ሂደት ነው። አጥፊው ወገን የግድ የዚህ ሂደት አካል መሆን የለበትም።»

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*