ከ‹አሸባሪዎች› መዳፍ ያልወጣው ክልል

ትግራይ ክልል ፈተና ለኢትጵያም ጭምር ነው። በፌዴራል መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ ይዞ ከስፍራው የሚሰሙ ዜናዎች መላው ኢትዮጵያውያንን ያሳስባል። ጦርነቱ በተጀመረ አጭር ቀናት ውስጥ ሕወሓት መሸነፉ ቢነገርም፤ ወደ ሽምቅ ውጊያ አምርቷል። ስለዚህ፣ ክልሉ አሁንም በከባድ የፀጥታ ችግር ውስጥ መሆኑ አይካድም። በዚያ ላይ የዓለም መንግሥታት ችግሩ እንዳይቀረፍ ጫና እየፈጠሩ ነው።

ድርጅቱ በአሸባሪነት እስኪጣራ ድረስ ድርድር ለማስቀመጥ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ሕወሓት ግን ከክልሉ አልፎ ለመላው ኢትዮጵያ የለየለት ሥጋት የሆነው ከለውጡ ወዲህ ነበር። በክልሉ የመንግሥት ሚዲያ የሚያሰራጨውን ጦርነት ቀስቃሽ አጀንዳ እና ደጋግሞ የሚያወጣውን መግለጫ የተመለከተ ሰው ይህ እንደሚፈጠር አይጠፋውም። ቀድሞ ቀሰቀሰው በተባለው ጦርነት የሚሞቱት ወገኖች እና የሚወድመው ሀብት እና ንብረት ከክልሉ ቀጥሎ የሚጎዳው አገሪቱን ነው።

ለነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች በጦርነቱ እየተማገዱ ነው። የሕግ ማስከበር ጦርነቱ በይፋ በተጀመረ ሰሞን ሕወሓት አሰለጠናቸው የተባሉ የልዩ ኃይል አባላት የትግራይ ታዳጊ ወጣቶች እንደነበሩ ይታወሳል። ይህ ጉዳይ ሕወሓት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሽምቅ ውጊያ ከገባ በኋላም አልቆመም። በግዳጅም ይሁን ጠቀም ያለ ገንዘብ በመክፈል የትግራይ ወጣቶችን ወደ ጫካ እየወሰደ ጦርነት እያለማመደ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*